በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ፖሊስ ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር የታፈሱ 13 ወጣቶች በገንዘብ ዋስትና ተፈተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 13 ቀን…

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ፖሊስ ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር የታፈሱ 13 ወጣቶች በገንዘብ ዋስትና ተፈተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ማርያም ሰፈር አካባቢ ከጥምቀት በዓል ጋር በተያያዘ “የፋኖን ስም በመጥራት ና በለው ሆ እያላችሁ ጨፍራችኋል” የተባሉ 13 ወጣቶች ጥር 13/2015 አመሻሹን በወረዳው ፍ/ቤት ቀርበው እያንዳንዳቸው በ200 ብር ዋስትና ከእስር ተፈተዋል። ከጆሞ 3 ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጥምቀትን አክብረው ወደ ሰፈራቸው ማርያም አካባቢ እየተመለሱ እያለ መታሰራቸው ይታወቃል። የማህበረ ስላሴ አባላትን ጨምሮ የፖሊስ አባላትና የመከላከያ ሰራዊት አባላት የታሰሩትም:_ 1) ዱላ ይዛችሁ ሆ እያላችሁ ጨፍራችኋል፣ 2) በጭፈራው መሀልም የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን እና አርበኛ መሳፍንት ተስፉን፣ የጄኔራል አሳምነው ጽጌን ስም በመጥራት ና በለው ፋኖ ብላችኋል፣ 3) ማህበረ ስላሴ አሳትሞ የለበሰውን ቲሸርት 7 ቁጥር ስላለው ብቻ ግንቦት 7 ናችሁ፣ 4) የማርያም ሰፈርን ባጅ ይዛችሁ ለምን ወደ ጆሞ 3 ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሄዳችሁ? የሚሉ እና መሰል ጥያቄዎችን በማንሳት በማርያም ሰፈር ባለ ፖሊስ ጣቢያ አስረዋቸዋል። ጥር 13/2015 እያንዳንዳቸው በ200 ብር ዋስትና ከእስር የተለቀቁትም:_ 1) ደመቀ አቤ፣ 2) ኃይሉ ቢምረው፣ 3) አዳሙ ቢምረው፣ 4) ግዛቸው አሰፋ፣ 5) ፖሊስ ስሜነህ ብድሬ፣ እየተማረ ያለ፣ 6) መርማሪ ፖሊስ ሙሉጌታ ሀብቴ፣ጊዜያዊ እረፍት ስላወጣ፣ 7) ተስፋው ተፈሪ፣ 8 ሲሳይ ባዬ፣ 9) ሰለሞን ምስጋናው፣ 10) ክፍሌ አባተ፣ 11) ሰውነት መኩ፣ 12) መሰለ ታከለ፣ 13) ሲሳይ ባዬ የተባሉ ነዋሪዎች ናቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply