በአዲስ አበባ ከተማ የማህበር ቤት ለመገንባት የወሰን ማስከበር ችግር የነበረባቸው መሬቶች ሙሉ በሙሉ እግዳቸው ተነሳ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ኃላፊ ፅጌወይን ካሳ ፤ ” የማህበር ቤት ለመገንባት የወሰን ማስከበር ችግር የነበረባቸው መሬቶች ሙሉ በሙሉ እግዳቸው ተነስቷል ” ብለዋል።

ማህበራቱም ግንባታቸውን መቀጠል እንደሚችሉ ኃላፊዋ ገልፀዋል።

በ40/60 እና በ20/80 ተመዝጋቢ የነበሩ እና በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የተዘጋጁ 57 ማህበራት በወሰን ማስከበር ምክንያት የግንባታ ስራቸው ላይ እንቅፋት እንዳጋጠማቸው የቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል።

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply