በአዲስ አበባ ከተማ የብዙሀን ትራንስፓርት አገልግሎት ከተጠቃሚው ጋር መጣጣም አልቻለም ተባለ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት የተገልጋዩ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ከትራ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/XwsHjrirJSytddhGk9tVggcwVRZ3ZRvfevsp3a5DvYpdyAQOuDqHw4HFngO5kzfZ_V3E4iJnln-Iywjlzu5jYJ5kgbu-FxIYUGLQhTOjCgdAVn0snkWmCbbtVYxDmjmIWYUSvG6mWZnvwnGcKHVpam5al89PVsbwuhJ8tx_cqo7c2GBAFEEzrIn3FmxJTEvPuW652Sa6WAU6oJhpZgy-YXalWsGkrhJtm6Gm05wanMvUywe5OxAEN3sxcsQ_sjnFPHGE9rhnLZuprjfgEDw0Y-lt-JKClvNBM9eu99qNTapnV4ePIPSg8pAdMYKRTzC6vbcBYMbJYlFXrR5kG3lpzA.jpg

በአዲስ አበባ ከተማ የብዙሀን ትራንስፓርት አገልግሎት ከተጠቃሚው ጋር መጣጣም አልቻለም ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት የተገልጋዩ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ከትራንስፖርት አቅርቦቱ ጋር አለመጣጣም እንደፈጠረ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

በተለይም የትራንስፓርት አገልግሎት እጥረት የስራ መግቢያ እና መውጫ ሰአቶች ላይ ችግሩ በሰፊው ይስተዋላል ተብሏል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የትራንስፖርት ቢሮው ኮምኒኬሽን ዳይሬክተር እፀገነት አበበ እጥረቱን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት እየሰራን ነው ብለዋል።

የመንገድ ኔትዎርኮችን ማስፈት ችግሩን ለመቀነስ መፍትሄ እንደሆነም ነው ያነሱት።

ከባለፈው በጀት አመት ጀምሮ 3 መቶ 77 የሚሆኑ አውቶብሶችን ወደ ስምሪት በማስገባት በተወሰነ ደረጃ ችግሮችን ለመፍታት መሞከሩንም አንስተዋል።

በሐመረ ፍሬው

ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply