#በአዲስ አበባ ከተማ የተቋቋመው የቤቶች አፍራሽ ግብረ ሃይል በኗሪዎች ላይ ከፍተኛ ግፍ እና በደል እየፈፀመነው ተባለ! ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአገዛዙ ይሁንታ የተቋቋመው…

#በአዲስ አበባ ከተማ የተቋቋመው የቤቶች አፍራሽ ግብረ ሃይል በኗሪዎች ላይ ከፍተኛ ግፍ እና በደል እየፈፀመነው ተባለ! ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአገዛዙ ይሁንታ የተቋቋመው የቤቶች አፍራሽ ግብረሃይል በርካቶችን ቤት አልባ አድርጎ ሜዳላይ የጣለ ሲሆን መብታቸውን የጠየቁትን ደግሞ እያዋከበ እና እያሰረ ይገኛል ሲሉ ተጎጂዎቹ ለአሻራ ሚድያ በስልክ ተናግረዋል። ከአፍራሽ ግብረሃይሉ ጋር ተከትሎ የሚመጣው ኦሮምኛ ተናጋሪ የታጠቀ ሃይል ቤታችን ከመፍረሱ በላይ ተኩሶ ገድሎናል፣ድብደባ እና እስርም እየፈፀመብን ይገኛል ሲሉም አብራርተዋል። ወለጋ እየተፈፀመ ያለው ግፍ እና በደል በአዲስ አበባ አማሮች ላይ እየተደገመ ነው፤ ያሉት ምንጮቻችን እስካሁን የፈረሱ ቤቶች በሙሉ የአማራ ተወላጆች ይኖሩባቸው የነበሩ ናቸው ብለዋል። በአገዛዙ ስርዓት ምክንያት ወልደን ያሳደግንበት ቤታችን ላያችን ላይ ፈርሶብናል።በሽምግልና እድሜያችን ከነልጆቻችን ጎዳና ላይ ተጥለናል ሲሉም ጨምረዋል። አክለውም የወለጋው ገዳይ ሃይል አዲስ አበባን ከተቆጣጣረ የቆየ ቢሆንም አሁን ግን ይፋ ወጠጥቶ በመዲናዋ አዲስ አበባ ውስጥ ሰዎችን በጠራራ ፀሃይ እየገደለ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል። በመጨረሻም ይህን አደገኛ አካሄድ የሚመለከተው አካል በጊዜ እልባት ካልሰጠው ሙሉ አዲስ አበባ ወለጋ ትሆናለች ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply