You are currently viewing #በአዲስ አበባ ከተማ የጥምቀት በዓልን ለማክበር በወጡ ወጣቶች ላይ ፖሊስ ድብደባ እና ወከባ መፈፀሙ ተገለፀ! ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ትናትና ጥር 11ቀን 2015 ዓ.ም…

#በአዲስ አበባ ከተማ የጥምቀት በዓልን ለማክበር በወጡ ወጣቶች ላይ ፖሊስ ድብደባ እና ወከባ መፈፀሙ ተገለፀ! ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ትናትና ጥር 11ቀን 2015 ዓ.ም…

#በአዲስ አበባ ከተማ የጥምቀት በዓልን ለማክበር በወጡ ወጣቶች ላይ ፖሊስ ድብደባ እና ወከባ መፈፀሙ ተገለፀ! ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ትናትና ጥር 11ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ዓለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቅዱስ ገብርል ታቦትን ሲያጅቡ የነበሩ በርካታ ወጣቶች አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ ይዛችኃል በሚል በወጣቶችላይ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች ለአሻራ ሚድያ በስልክ ተናግረዋል። አረንጓዴ ቢጫቀይ ሰንደቅ አላማ የፋኖ ባንዲራ ነው ። የነፍጠኛን ባንዲራ ማየት አንፈልግም በማለት ግባራቸው ላይ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያሰሩትን ሁሉ ሲደበድቡ እናሲያዋክቧቸው መዋላቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል። በተጨማሪም ጥምቀት ከመድረሱ ከ3 ቀን በፊት ጀምሮ ወጣቶች በዓሉን በነፃነት እንዳያከብሩ ሆን ተብሎ ፖሊስ ካለምንም ምክንያት ሲያስር እና ሲያክብ የቆየ መሆኑን ገልፀው በዓሉን በማክበር ላይ ያሉ ወጣቶችን ድብደባ ፈፅመውባቸዋል ብለዋል። ትናንት ማለትም ጥር 11 ቀን 2015 ዓ.ም በርካታ ወጣቶች ባህላዊ ጭፈራዎችን እና የተለያዩ ባህላዊ ትዕይንቶችን እያሳዩ በነበሩበት ሰዓት በፌድራል ፖሊስ የታጀቡ የካሜራ ባለሙያወች ቦታው ላይ በመገኘት ፎቶ እንዳነሱቸውም ገልፀው ይህን ያደረጉበት ምክንያት ለቀጣይ አፈና እንዲመቻቸውነው ሲሉ አብራርተዋል። አዲስ አበባ ውስጥ ማንነትን መሰረት ያደረገ በኦህዴድ ይሁንታ እየተካሄደ ያለው ህገወጥ አፈና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መቀጠሉንም አክለው ገልፀዋል።በተለይም በወጣቶች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እና በደል የሚያስቆመው አጧል።መንግስት በጊዜ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply