በአዲስ አበባ ከተማ 6ኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራ ትላንት ተጀምሯል።
በ6ኛ ዙር በተመረጡ በሰባት ክፍለ ከተሞች ከግንቦት 03/09/2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ ተከታታይ አምስት ወራት 50 ሺህ የመሬት ይዞታዎችን የማረጋገጥ ስራ ይካሄዳል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታውቋል።
ኤጀንሲው ምዝገባው ፦
👉 በኮልፌ ቀራኒዮ፣
👉 በቂርቆስ፣
👉 በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣
👉 በቦሌ፣
👉 በአዲስ ከተማ፣
👉 በልደታና በአራዳ ክፍለ ከተሞች ባሉ 50 ቀጠናዎችና 211 ሰፈሮች እንደሚከናወን ገልጿል።
ይህ የይዞታ ማረጋገጥ እወጃ ከተላለፈ ከ15 ቀናት በኃላ የይዞታ ይረጋገጥልኝ ጥያቄዎች በክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤቶች ቀርበው ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይቻላል ተብሏል።
ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ በተመረጡ ቀጠናዎችና ሰፈሮች ስራው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ባለቱ አምስት ወራት ውስጥ የመረጃ ልዩነት እንዳይፈጠር ሲባል ምንም ዓይነት የስመ- ንብረት ዝውውር አገልግሎት እንደማይሰጥ ኤጀንሲው ማስታወቅን ከአ/አ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።