በአዲስ አበባ ከተሰማሩ 500 ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ውስጥ 200ዎቹ ስራ አቆሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ…

በአዲስ አበባ ከተሰማሩ 500 ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ውስጥ 200ዎቹ ስራ አቆሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ያለውን የትራንስፖር እጥረት ለመቅረፍ በሚል ድጋፍ እንዲሰጡ 500 አውቶቡሶችን ወደ ስራ ማስገባቱ ይታወሳል። ከነዚህ ውስጥም 200 የሚሆኑት ስራ ማቆማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሚውኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናረዋል፡፡ እርሳቸው እንዳሉት ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶቹ በመኖራቸው አንፃራዊ የትራንስፖርት መጨናነቁን ቀንሰውት ነበር ያሉ ሲሆን አሁን ግን ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለአንዳንድ ስራ በመፈለጋቸው 200 የሚሆኑት ድጋፋቸውን አቁመዋል ብለዋል፡፡ ስለዚህም አሁን ላይ እንደከዚህ ቀደሙ በዋናነት ምልልሱን እየሰሩ ያሉት 300 የሚሆኑት አውቶቡስ በመሆናቸው ከተማው ላይ እየተስተዋለ ላለው የትራንስፖርት እጥረት እንደዋና ምክንያት ሆኗል ብዋል፡፡ ከዛም በተጨማሪም ከሁለት ሳምንት በፊት ትምህርት ቤቶች መከፈታቸውም የትራንስፖርት እጥረቱ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩን ተናግረዋል። ይሁንና ካለፈው ቅዳሜ ጠዋት አንስቶ በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች ሰማያዊ ታክሲዎች ከተለመደው ባነሰ መልኩ መኖራቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ታዝቧል። አንዳንድ የታክሲ አሽከርካሪዎች ለማናገር እንደሞከርነው መንግስት በነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ መኖሩ መስራት እየከበዳቸው መሆኑን ነግረውናል። አቶ አረጋዊም ለዚህ ሀሳብ በነዳጅ መሸጫ ታሪፍ ጭማሪ ምክንያት እጥረቱ ሊከሰት ይችላል ብለው እንደማያስቡ አቶ አረጋዊ ተናግረዋል። የትራንስፖርት ቢሮው ምንአልባት የታሪፍ ለውጥ የሚያስፈልገውም ከሆነ ጥናት ተካሂዶበት በአሽከርካሪዎች ላይ እና በባለቤቶቹ ላይ ተፅዕኖ የሚያመጣ ከሆነ በሚመለከተው አካል ታይቶ ማሻሻያ ሊደረግ ይችላል ብለዋል። ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply