
ሰሚት ኮንዶሚኒየም ብሎክ 240 ውስጥ ነው የተፈጸመው። ረፋድ ላይ አሠሪዋ “ከቤት እቃ ጠፍቷል፤ የት አለ?” ይላታል። ምንም እንደማታውቅ ትናገራለች። አሠሪዋ ግን “አላውቅም” ማለቷን ሳይቀበል ይደበድባት ጀመር። የልጅ አካሏ ከሚችለው በላይ ስትደበደብ ራሷን ሳተች። አሠሪዋ ውሃ ሲያፈስባት ነቃች። ድብደባው እንደማያቋርጥ የተገነዘበችው ብርቱካን ነፍሴን ባድን ብላ ከቤቱ ሮጣ ወጥታ ከአራተኛ ፎቅ ወደ ምድር ተወረወረች።
Source: Link to the Post