በአዲስ አበባ ከኦሮሚያ ክልል ባንዴራ እና መዝሙር ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ከአዲስ ከተማና የካቲት አካባቢ ካሉ ት/ቤቶች ተወስደው የታሰሩ ተማሪዎች ቁጥራቸው ከፍተኛ መ…

በአዲስ አበባ ከኦሮሚያ ክልል ባንዴራ እና መዝሙር ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ከአዲስ ከተማና የካቲት አካባቢ ካሉ ት/ቤቶች ተወስደው የታሰሩ ተማሪዎች ቁጥራቸው ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ፤ ለስብስባ ይፈለጋሉ በሚል ወደ ቂርቆስ ክ/ከተማ ተወስደዋል በመባሉ አግኝተን ለመጠየቅ አልቻልንም ሲሉ የተማሪ ወላጆች ተናግረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ የተለያዩ ት/ቤቶች የኦሮሚያ ክልል ባንዴራ እንዲሰቀል እና የክልሉ መዝሙርም እንዲዘመር በኃይል ተጽዕኖ ተደርጎብናል ያሉ ተማሪዎች ተቃውሞ ማቅረባቸውን ተከትሎ በርካታ መምህራንና ተማሪዎች ለእስር እየተዳረጉ ነው። በአዲስ ከተማ እና በየካቲት አካባቢ ባሉ ት/ቤቶችም ከኦሮሚያ ክልል ባንዴራ እና መዝሙር ጋር በተያያዘ በተለይም ከታህሳስ 3/2015 ጀምሮ በርካታ ተማሪዎች መታሰራቸውን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ገለጹት የተማሪዎች ወላጆች ናቸው። አብዛኞቹ ተማሪዎች በእስር ላይ የሚገኙት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በአራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ነው። በጊዜ ቀጠሮ ላይ ያሉ ተማሪዎች የሚቀርቡት አዲሱ ሚካኤል ፊት ለፊት ባለ ፍ/ቤት ሲሆን መደበኛ ክስ የሚመሰረትባቸው ከሆነ ደግሞ አማኑኤል አካባቢ ባለው ፍ/ቤት መሆኑ ተገልጧል። ወደ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ልጆቻቸውን ለመጠየቅ ታህሳስ 8/2015 ጠዋት ላይ መሄዳቸውን የገለጹት ወላጆች ቂርቆስ ክ/ከተማ ለውይይት እንፈልጋቸዋለን በሚል በእስር ላይ የነበሩ ተማሪዎች እንደተወሰዱ ተነግሮናል ብለዋል። ከ50 ያላነሱ ተማሪዎች እንዲሁም ከኦሮሚያ ባንዴራ ጋር በተያያዘ በርካታ የአዲስ አበባ ወጣቶች በአራተኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ እንዳሉም አሚማ ለማወቅ ችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply