በአዲስ አበባ ከ700 ሺህ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች የዲጅታል መታወቂያ ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ። እስካሁንም ለ140 ሺ የከተማዋ ነዋሪዎች ይህ ዲጂታል መታወቂያ መሰጠቱን ኢትዬ ኤፍ ኤ…

በአዲስ አበባ ከ700 ሺህ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች የዲጅታል መታወቂያ ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ።

እስካሁንም ለ140 ሺ የከተማዋ ነዋሪዎች ይህ ዲጂታል መታወቂያ መሰጠቱን ኢትዬ ኤፍ ኤም ከከተማዋ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ሰምቷል።

የ አዲስ አበባ ወሳኝ ኩነትና ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ዶክተር ታከለ ነጫ እንዳሉት ይህንን ዲጅታል የነዋሪዎች መታወቂያ በ96 ወረዳዎች ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።

ኤጀንሲው ባለፉት ሶስት ወራት ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብንም አስታውቋል።

አሰራሩን ለማዘመን የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ፣የፎርጅድ ሰነዶች መበራከት፣እንዲሁም በየወረዳው ያሉ አንዳንድ የኤጀንሲው ሰራተኞች ህገ ወጥ ተግባር ላይ መሳተፍ ለወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎቱ እንቅፋት መሆኑ ተነግሯል ።

በተጨማሪም በከተማዋ በአንድ ሰው መኖሪያ ቤት ከ50 ሰው በላይ የነዋሪነት መታወቂያ እንደሚወጣም ተነግሯል።

በከተማዋ የሚገኙ አንዳንድ ነዋሪዎች በየመኖሪያ ቤታቸው ያሻቸውን መታወቂያ ያለ ገደብ በማሶጣት የነዋሪነት መታወቂያውን የገቢ ምንጭ ማድረጋቸውም ተሰምቷል።

የነዋሪነት መታወቂያውን ከ 2 ሺ ብር ጀምሮ እስከ 7 ሺ ብር ድረስ በህገ ወጥ መንገድ ሲሰጡ የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውንም ዶክተር ታከለ ተናግረዋል።

በየውልሰው ገዝሙ
ሕዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply