#በአዲስ አበባ ወ/ሮ ቀለም ወርቅ መሠናዶ ት/ቤት ግጭት መነሳቱ ተገለፀ! ታሕሳስ 6 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ ት/ቤት እንደ…

#በአዲስ አበባ ወ/ሮ ቀለም ወርቅ መሠናዶ ት/ቤት ግጭት መነሳቱ ተገለፀ! ታሕሳስ 6 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ ት/ቤት እንደ አዲስ አጀንዳ አስይዘው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሰንደቅ አላማ እንዲውለበለብና የክልሉ መዝሙር በሚል በተማሪወችና በመምህራን መካከል ግጭት በመነሳቱ የሰው ህይወት መጥፋቱ ይታወሳል። በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ሰሜን ማዘጋጃ “ወ/ሮ ቀለምወርቅ መሠናዶ ትምህርት ቤት “የኦሮሞን መዝሙር አንዘምርም፤ጨርቁንም አንሰቅልም” በሚል ተማሪዎች ዛሬ እንቢ በማለታቸው የታጠቁ ኃይሎች ወደ ተማሪዎች ጥይት በመተኮሳቸው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተማሪወች መቁሰላቸውን የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ለአሻራ ተናግረዋል ። እንዲህ ይላሉ “እኛ አዲስ አበቤዎች ያለን አንድ ከተማ፣ ሀገራችን ደግሞ ኢትዮጵያ ናት፤በተረኝነት የተጫንንብን አዲስ ማንነት አንቀብልም ብለዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply