
በአዲስ አበባ ዙሪያ ለገጣፎ አቦ ሰፈር እና ቄስ ሰፈር በኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት በታጀበ አፍራሽ ግብረ ኃይል እና በእስካቫተር የዜጎች ቤት ዛሬም ሲፍርስ ውሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 7 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ዙሪያ ለገጣፎ አቦ ሰፈር እና ቄስ ሰፈር የካቲት 7/2015 በበርካታ ፓትሮል የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት በታጀበ የኦሮሚያ አፓርታይዳዊ አገዛዝ አፍራሽ ግብረ ኃይል እና በእስካቫተር የዜጎች ቤት ዛሬም ሲፍርስ ስለመዋሉ ተጎጅዎች ተናግረዋል። አዲስ አዋቅረነዋል ባሉት “ሸገር ሲቲ” የተለያዩ አካባቢዎች ተጠናክሮ የቀጠለው ማንነትን መሰረት ባደረገው ቤት የማፍረስ ዘመቻ የአማራ ተወላጆች በከፍተኛ ቁጥር እና ደረጃ ተጎጅዎች ናቸው። ቤት የማፍረስ ዘመቻውም የሀሰት ትርክት የወለደው የኖረ ጥላቻን መሰረት አድርጎ እየተፈጸመ በመሆኑ ከፍተኛ የአማራ ተወላጆች ቁጥር ባለበት ጥናት ተደርጎ እንደሚፈጸም የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች እየተናገሩ ነው። ስናይፐር፣ መትረጊዬስና ክላሽ በያዙ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እየታጀበ ከሰብአዊነት፣ ከሞራል፣ ከፍትህ እና ከህግ ባፈነገጠ መልኩ በተደራጀ መልኩ እየተፈጸመ ባለው የቤት ማፍረስ ብሎም በኢኮኖሚ የማድቀቅ፣ ሁለንተናዊ እረፍት የመንሳት ዘረኛ አካሄድ በሽህ የሚቆጠሩ ወገኖች ሜዳ ላይ እንዲወድቁ እየተደረገ ነው። እንደተለመደው ሰሚ እያገኙ ባይሆንም ዛሬም ተስፋ ባለመቁረጥ የድረሱልን ጥሪ እያቀረቡ ነው።
Source: Link to the Post