በአዲስ አበባ ዙሪያ ሱሉልታ ከተማ ከህግ ውጭ የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 7 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚ…

በአዲስ አበባ ዙሪያ ሱሉልታ ከተማ ከህግ ውጭ የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 7 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተመሰረተዉ በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱሉልታ ከተማ ልዩ ስሙ ቃሶ በተባለዉ አካባቢ፣ ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳስታወቁት፣ ልዩ ስሙ ቃሶ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ “መጤ ናችሁ በሚል ቤታችን እየፈረሰብን ነዉ” ብለዋል፡፡ ቤት ንብረት አፍርተዉ በአካባቢዉ መኖር ከጀመሩ ከ5 አመት እስከ 10 አመት ድረስ እንደሆናቸዉ የተናገሩት ነዋሪዎቹ ያለንም ማስጠንቀቂያ ቤታቸዉ እንደፈረሰ ነግረዉናል፡፡ ዜጎቹ የሚመለከተዉ አካል እንዲያስቆምላቸዉ ቢጠይቁም ምላሽ እንዳልተሰጣቸዉ ገልፀዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸዉን አንስተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የአካባቢዉ የደንብ አካላት የሚፈርሱ ቤቶችን እየለዩ መሆናቸዉንም ሰምተናል፡፡ በመሆኑም መንግስት በአስቸኳይ ይድረስልን ሲሉ ጥሪያቸዉን አሰተላልፈዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ምላሽ እንዲሰጠን ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡ ኢትዮ ኤፍ ኤም እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply