በአዲስ አበባ ዙሪያ በአዲሱ አጠራር “ሸገር ሲቲ” ሱልልታ ቻይና ጋራጅ አካባቢ ቀለም ተቀብቷል፤ ሊፈርስባቸው መሆኑ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ/ም…

በአዲስ አበባ ዙሪያ በአዲሱ አጠራር “ሸገር ሲቲ” ሱልልታ ቻይና ጋራጅ አካባቢ ቀለም ተቀብቷል፤ ሊፈርስባቸው መሆኑ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ዙሪያ በአዲሱ አጠራር “ሸገር ሲቲ” ሱልልታ ሚዛን በተባለ አካባቢ የካቲት 1/2015 ከ1ሽህ ያላነሰ የነዋሪዎችን ቤት በማፍረስ ዜጎችን ሜዳ ላይ ጥለዋል። በኦሮሞ ታጣቂዎች ታጅበው የሚመጡ የአፍራሽ ግብረ ኃይል አባላት ዜጎች ለብዙ ዓመታት ገንብተው የሚኖሩበትን በጭካኔ በማፍረስ ተግባር ተጠምደዋል። እንደ ስራ እድል ፈጠራ እና በዝርፊያ ጭምር የገቢ ምንጭ ማግኛ መንገድ አድርገው ስለሚጠቀሙበት በርካታ ስራ አጥ ወጣቶችን አደራጅተው በማስገባት የነዋሪዎች ቤት እንዲፈርስ እያደረጉ ነው። የአካባቢውን ቤቶች የዛሬ አራት ዓመት ለማፍረስ ተሞክሮ በወቅቱ የነበረውን የህዝብ ጭሆት እና ለቅሶ ተከትሎ ለጊዜው ማፍረሱ እንዲቋረጥ የተደረገበት ነበር። ወደ አረብ ሀገር ተሰደው ጥረው ግረው ባገኙት ገንዘብ ከገበሬዎች መሬት ገዝተው ቤት ገንብተው ለብዙ ዓመታት የሚኖሩ ዜጎች ዋነኛ የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል። በተያያዘ በለገጣፎ ገዋሳ ልዩ ስሙ ክፍሌ እንጨት ቤት አካባቢ ጥር 30 እና የካቲት 1/2015 በርካታ ቤቶችን እያፈረሱ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply