You are currently viewing በአዲስ አበባ ዙሪያ አዲስ በተመሰረተው የሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ  ከሰብዓዊነት ያፈነገጡ ተግባራት እየተፈጸሙ እንደሚገኙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በአዲስ አበባ ዙሪያ አዲስ በተመሰረተው የሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ከሰብዓዊነት ያፈነገጡ ተግባራት እየተፈጸሙ እንደሚገኙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በአዲስ አበባ ዙሪያ አዲስ በተመሰረተው የሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ከሰብዓዊነት ያፈነገጡ ተግባራት እየተፈጸሙ እንደሚገኙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በቅርቡ በተመሰረተውና ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ነው በተባለው ሸገር ከተማ ስር በተካተቱ ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ሱሉልታ እና ገላን በተባሉ አከባቢዎች ዜጎች ለአመታት የኖሩባቸው መኖሪያ ቤታቸው ፈርሶባቸው ሜዳ ላይ መውደቃቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች በሳምንት ውስጥ መፍረሳቸን የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለአመታት ያፈሩት ሃብትና ንብረት በደቂቃዎች ውስጥ ወደ አፈርነት ከመቀየሩም ባለፈ ያልተገቡ ድብደባና ማዋከቦች እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ አስረድተዋል። መድረሻ ያጡ ዜጎችም በመስጊድ፣ በቤተክርስቲያን እና በሜዳ ላይ ተጠልለው እንደሚገኙ ነው የሚገልጹት። በአዲስአበባ ዙሪያ አዲስ በተመሰረተው የሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ከሰብዓዊነት ባፈለገጠ መልኩ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እምባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ተናግረዋል። “ሲሆን አገራት ለዜጎቻቸው ቤት ሰርተው ይሠጣሉ” የሚሉት ዋና የህዝብ ዕንባ ጠባቂው ዜጎች ጥሪታቸውን አሟጠው የሠሩትን ቤት ያለበቂ ካሳና መጠለያ በማናለብኝነት ማፍረስ ከመንግስት የሚጠበቅ ተግባር አለመሆኑን ተናግረዋል። እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ዜጎችን በአገራቸው ባይተዋርና ስደተኛ የሚያደርግ ነዉ ብለዋል። በሂደቱም ከገበሬ የተገዙና ካርታ ከሌላቸው ውጪ ካርታ ያላቸውን ህጋዊ ቤቶች ጭምር እየፈረሱ መሆናቸው ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል ሲል ኢትዮ መረጃ ኒውስ አጋርቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply