በአዲስ አበባ ዙሪያ ከለገጣፎ የተለያዩ አካባቢዎች በማንነታቸው ብቻ ለዘመናት የሚኖሩበት ቤታቸው በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ የፈረሰባቸው አማራዎች የድረሱልን ጥሪ ለማቅረብ ወደ ደብረ ብርሃን…

በአዲስ አበባ ዙሪያ ከለገጣፎ የተለያዩ አካባቢዎች በማንነታቸው ብቻ ለዘመናት የሚኖሩበት ቤታቸው በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ የፈረሰባቸው አማራዎች የድረሱልን ጥሪ ለማቅረብ ወደ ደብረ ብርሃን መጓዛቸው ታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ዙሪያ ከለገጣፎ የተለያዩ አካባቢዎች በማንነታቸው የተነሳ ለዘመናት የሚኖሩበት ቤታቸው በኦህዴድ ብልጽግና ዘረኛ አገዛዝ በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች እንደፈረሰባቸው ተናግረዋል። በተለይም ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ አሁንም ድረስ ተጠናክሮ በቀጠለው የኦሮሙማው ቤት የማፍረስ ሂደት ምንም እንኳ ሰፊው የጉዳቱ ሰለባ አማራዎች ይሁኑ እንጅ ከኦሮሞ ተወላጆች ውጭ እንደአብነት የጉራጌ፣ የጋሞ፣ የወላይታ፣ የስልጤ፣ የትግሬ እና የሌሎች ኢትዮጵያዊያንም ቤት በግብረ ኃይል እና በእስካቫተር በመፍረሱ ለከፋ ጉዳት ተዳርገዋል። ይህን ተከትሎ የሚሰማቸው አጥተው በአማካይ አስር ዓመት እና ከዛም በላይ ገንብተው የኖሩበት ቤታቸው ከፈረሰባቸው በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች መካከል ከ200 በላይ የሚሆኑት ከየካቲት 15/2015 ጠዋት ጀምሮ ለአቤቱታ ወደ ደብረ ብርሃን አቅንተዋል። ሜዳ ላይ የወደቁት እነዚህ ተጎጅዎች የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሚችለውን ያህል ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ለመጠየቅ ነው ወደ አካባቢው ያቀኑት። የአማራ ክልል መንግስት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም እንዲረከቧቸውም የድረሱልን ጥሪ ለማቅረብ መጓዛቸውን ተወካዮቻቸው ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply