You are currently viewing በአዲስ አበባ ዙሪያ ጣፎ ቃርሳ ደብረ ሰላም እና ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ጥቁር የለበሱ አባቶች እና ምዕመናን በኦሮሞ ሚሊሾች ታፍነው ተወሰዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በአዲስ አበባ ዙሪያ ጣፎ ቃርሳ ደብረ ሰላም እና ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ጥቁር የለበሱ አባቶች እና ምዕመናን በኦሮሞ ሚሊሾች ታፍነው ተወሰዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በአዲስ አበባ ዙሪያ ጣፎ ቃርሳ ደብረ ሰላም እና ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ጥቁር የለበሱ አባቶች እና ምዕመናን በኦሮሞ ሚሊሾች ታፍነው ተወሰዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ዙሪያ ጣፎ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ጋር ቆይታ ያደረጉ አባቶች ከጣፎ ቃርሳ ደብረ ሰላም እና ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን አባቶች እና ምዕመናን በኦሮሞ ሚሊሾች ታፍነው ተወስደዋል። በምዕመናን ላይ የአፈና ድርጊቱ የተፈጸመው ጥር 29/2015 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ መሰረት በቤተ ክርስቲያን የነነዌ ምህላ ጸሎት እያደረጉ ባሉበት ድንገት ከበባ ባደረጉ የኦሮሞ ሚሊሾች ነው። አንዲት እናት ጥቁር ለብሷል ተብሎ ታፍኖ ከተወሰደው ከ8 ዓመት ልጃቸው ተለይተው እያለቀሱ ተስተውለዋል። የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደር ጨምሮ አራት ካህናት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ወደ ሚሽን ፖሊስ ጣቢያ ስለመወሰዳቸው ተገልጧል። በግፍ ታፍነው የተወሰዱትም:_ 1) መላከ ሰላም ቄስ ኪሮስ ዘውዱ፣ በቃርሳ ደብረ ሰላም እና ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ 2) ቄስ ደርበው፣ 3) ቄስ ስመኘው እና 4) ቄስ ለይኩን እና ህጻን ያዘሉ እናቶች ሳይቀሩ በአገዛዙ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል። የታፋኝ ቤተሰቦችም በከፍተኛ ጭንቀት ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ድረሱልን ሲሉ ተማጽነዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply