You are currently viewing በአዲስ አበባ የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ አባል እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለ ደሬ ወረዳ የመኢአድ እጩ ተወዳዳሪ መምህር መሀመድ ይማም እና 4 ሰዎች በዋስትና ከእስር ተፈተዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕ…

በአዲስ አበባ የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ አባል እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለ ደሬ ወረዳ የመኢአድ እጩ ተወዳዳሪ መምህር መሀመድ ይማም እና 4 ሰዎች በዋስትና ከእስር ተፈተዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕ…

በአዲስ አበባ የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ አባል እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለ ደሬ ወረዳ የመኢአድ እጩ ተወዳዳሪ መምህር መሀመድ ይማም እና 4 ሰዎች በዋስትና ከእስር ተፈተዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 5/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ አባል እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለ ደሬ ወረዳ የመኢአድ እጩ ተወዳዳሪ መምህር መሀመድ ይማም እና 4 ሰዎች እያንዳንዳቸው በአስር ሽህ ብር ዋስትና ከ2 ሳምንት የእስር ቆይታ በኋላ ግንቦት 4/2015 ከእስር ተፈተዋል። በመጋቢት /2015 በሀይቅ ከተማ የተደረገውን ሰልፍ አስተባብራችኋል በሚል ታስረው በሀይቅ ማ/ቤት ታስረው ቆይተዋል። መምህር መሀመድ ይማም በሀይቅ ከተማ ከንግድ ቦታው ባለበት 4 ፖሊሶች ሚያዝያ 21/2015 ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ መጥተው በባለቤቱ እና በጎረቤቶች ፊት በመሳሪያ ሰደፍ እና በዱላ በቡድን የደበደቡት ቢሆንም ህክምና ተከልክሎ ነው የቆየው፤ አሁን ላይ ለህክምና መዘጋጀቱ ታውቋል። ቤተሰብ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ እንዲፈቱ ለደቡብ ወሎ ዞን ዐቃቢ ህግ አቤቱታ ማቅረቡን ተከትሎ በዋስ የተፈቱትም፦ 1. መምህር መሀመድ ይማም እንዲሁም 2. ዘርዓይ እንድሪስ፣ 3. እንድሪስ አሊ እና 4. ብርሃን አበራ የተባሉ የመስኖ ፕሮጀክት ኃላፊዎች ሲሆኑ 5. ውብሸት ገ/ጻዲቅ ደግሞ የፋኖ አባል ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply