በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ህንፃ እንደሆነ የሚነገርለት እየሩሳሌም መታሰብያ ህንጻ እየፈረሰ ነው፡፡ከ60 አመት በላይ ያስቆጠረው እየሩሳሌም መታሰብያ ህንፃ እየፈረሰ እንደሚገኝ ኢትዮ ኤፍ ኤም…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Pn8CF-OqgNHhketNDjzw_wPNFqKV7MUP6zqzrqwthEMS8xsFOw_JaY6WujYkx71aIRsNd_wqIG7ACg93tV7UT0PL2gWm5K6v8nhf434QeIwxnFt5mVwsP1PfQdmLdaM836TYdLzP4snXXuogdAc5ETDjeMZ1Zofd6cPVdnVSyqgZ1uk9pn95E58s8TUu53kRcBd4m4-Q042m4BuVkIRrSrF_9GsUui53lVGTDfwU2fyT-PQldTI2Mad3FPyeDjEJETFWBsiwkwsBt9A-lDLpLP0Pq6Vle8dVhd2LtHg7FNLJHHjByd2lRrwCy77gqxZRBdkLZ_maRUdY4Jid1t455g.jpg

በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ህንፃ እንደሆነ የሚነገርለት እየሩሳሌም መታሰብያ ህንጻ እየፈረሰ ነው፡፡

ከ60 አመት በላይ ያስቆጠረው እየሩሳሌም መታሰብያ ህንፃ እየፈረሰ እንደሚገኝ ኢትዮ ኤፍ ኤም በቦታው ተገኝቶ አረጋግጧል፡፡
የካቲት 16 ቀን 1956 አመተ ምህረት እንደተሰራ የሚገረው በአዲስ አበባ የመጀመርያ የነበረው እየሩሳሌም መታሰብያ ህንጻ ከፒያሳ እድሳት ጋር በተያያዘ ነው እየፈረሰ ያለው ተብሏል፡፡

ፒያሳ የሚገኝው ዕድሜ ጠገቡና በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ህንፃ ላለፉት በርካታ አመታት ህገመንግስት አጣሪ አጣሪ ጉባኤ በዋና መስራቤትነት ሲጠቀምበት ቆይቷል፡፡

ከህንፃው አናት ላይ በሠማያዊ ቀለም በደማቁ ተጽፎ ይታይ የነበረው የህንጻው ስም ማለትም እሩሳሌም መታሰብያ ህንጻ ይል የነበረው ሙሉ በሙሉ ተፈቅፍቆ መነሳቱ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያረጋገጠ ሲሆን የህንጻው መስታወቶች እና በር እና መስኮቶቹ በሙሉ ተነስተዋል፡፡

እንደዚሁም የጣራ ቆርቆሮዎች እና እና ብረታ ብረቶች በሙሉ ከህንጻ ተነስተው ለፈረሳ ዝግጁ መሆኑንም ታዝነበናል፡፡
ህንጻው ለማፍረስ የተዘጋጁ አፍራሽ ማሽኖች እና ገልባጭ መኪኖችም በህንጻው ዙሪያ ተርታቸውን ይዘው መቆማቸውን ጣበያችን በምልከታው ታዝቧል፡፡
ከቀናቶች በፊት ከማዘጋጃ ቤት ፍት ለፊት የነበረው የኢትዮ ቴሌኮም ህንጻ መፍረሱ አይዘነጋም፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply