በአዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን ትምህርት ቢሮ ባደረገው ሽግሽግ ላይ ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ከ…

በአዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን ትምህርት ቢሮ ባደረገው ሽግሽግ ላይ ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከአንዱ ወደ ሌላኛው ክፍለ ከተማ ባደረገው የመምህራን ሽግሽግ ላይ ቅሬታ እንዳደረባቸው ገልጸዋል። ትምህርት ቢሮው ባደረገው ሽግሽግ ቅሬታ አለን የሚሉት መምህራኑ፣ እስከ ዛሬ ከአንድ ትምህርት ቤት ወደ ሌላኛው ትምህርት ቤት ዝውውር ሲያደርጉ በፍላጎታቸው መሠረት አመልክተውና ተገቢውን ዝግጅት አድርገው ይፈጸም እንደነበር አውስተዋል። አሁን ላይ ግን እየሆነ ያለው በተቃራኒው እየተተገበረ ስለመሆኑ ነው አዲስ ማለዳ የዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply