በአዲስ አበባ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/PLWkfVqwNTQHpVCYkU_o8ToH8tbSnznKl4N8SqhCa6hriLYCnyjFwRPEb7Ck3HuKYNFCzggynGFgU9h04qHKf593aT8xM8rIkaAUoDrAxcyRSbeB-8fUXX7NuQBxhWfNuR8JFNSJR5iEa3EG3RpGdVlxRTCFKUuoxvX3uVaC-m0B0eLwxqQEaQBL0zuwIX0qAo4MigWtX3YAUL3uIxHkHhYjioG9OeoL2rbz_3yKMkAF_LdNzrxDboLrpntHdrtiicyBb2Y3-TUF0wxXdpwOg4ZLR-7yeE0jm7AGYvKAz0MrUkPX9TW7OqOTe9-lxnVmibbf7B0qMOROT2NtVvB1jQ.jpg

በአዲስ አበባ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጥሏል፡፡

ወቅቱ የፋሲካ በዓል በመሆኑ ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ስለሚኖር፣ ግርግር እና ስርቆት እንዳይፈጠር በማሰብ፤ አዲሱ ጥናት ተጠናቆ እስኪጠናቀቅ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ ቁጥጥር እንዲደረግ እገዳ ተጥሏል፡፡

በዚህም እርምጃ እንዲወሰድ ቢሮው ለሚመለከተው አካል የስራ ትዕዛዝ ማስተላለፉም ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሚያዝያ 06 ቀን 2014 ዓ.ም

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply