
በአዲስ አበባ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጸጥታ አካላትን ሰበብ እየፈጠሩ ማሰር እና ማሳደዱ የቀጠለ ስለመሆኑ ተነገረ። መጋቢት 09 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአዲስ አበባ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጸጥታ አካላትን ሰበብ እየፈጠሩ ማሰር፣ ማሳደዱ እና ማዳከሙ የቀጠለ ስለመሆኑ የተናገሩት የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የመረጃ ምንጮች ከተማ አስተዳደሩ የተሳሳተ መንገድን እየተከተለ ነው ሲሉ ወቅሰዋል። ለዚህም እንደማሳያ ከብዙ በጥቂቱ ከመርካቶ በኢ/ር እሱባለዉ ጌትነት እና ከእፎይታ በኮንስታብል አበበ ተሰራ ላይ የተፈጸመውን እስር ጠቅሰዋል። የኢ/ሩ የእጅ ስልኩ ፎረንሲክ ገብቶ እየተፈተሽ ስለመሆኑ የገለጹ ሲሆን ይህም በራስ አለመተማመንን ያሳያል ነው ያሉት። ኢንስፔክተር እሱባለው ጌትነት ከበደ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የገቢዎች እና ግምሩክ ወንጀል ምርመራ ማስተባባሪያ ኃላፊ ሲሆን መጋቢት 4/2015 ተይዞ መታሰሩ ተሰምቷል። በመርካቶ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኘው ኢ/ር እሱባለው መጋቢት 6/2015 አማኑኤል አካባቢ ባለው ፍ/ቤት ቀርቦ ለፊታችን ሰኞ መጋቢት 11/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል። ከተነሱበት ጉዳዮች መካከልም ብጥብጥ እና ሁከትን ማነሳሳት የሚለው ይገኝበታል። በስልክ ምርመራ ላይም ከተነሱበት ጉዳዮች መካከል:_ ከ2 ዓመት በፊት በፈረንጆቹ በ2021 አማራ ሚዲያ ማዕከል የዘገበውን ሼር አድርገሃል፣ ቴዲ አፍሮ ልሙጡን ባንዴራ ይዞ የዘፈነውን ሼር እና ላይክ አድርገሃል ስለመባሉ ችሎቱን የተከታተሉ ምንጮች ተናግረዋል። በተመሳሳይ በእፎይታ ፖሊስ ጣቢያ የሚሰራው ኮንስታብል አበበ ተሰራም በወቅታዊ ሀይማኖታዊ ጉዳይ በሚል ተጠርጥሮ የተያዘ ሲሆን መጋቢት 6/2015 ፍ/ቤት ቀርቦ ለፊታችን ማክሰኞ መጋቢት 12/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበብ እየፈጠረ የአማራ የጸጥታ አካላትን ለማዳከም እየሄደበት ያለው አሰራር በዘላቂነት ለማንም ስለማይጠቅም ሊወገዝ ብሎም በአስቸኳይ ሊስተካከል ይገባዋል የሚል ጥሪም ቀርቧል። ዘገባው የአሚማ ነው ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post