በአዲስ አበባ የአደጋ ደህንነት መስፈርት አሟልተዉ የተገኙ 33 ተቋማት ብቻ መሆናቸው ተገለጸ።

በመዲናዋ ከሚገኙ የተለያዩ ተቋማት መካከል የአደጋ ደህንነት መስፈረት አሟልተው የብቃት ማረጋገጫ የወሰዱት 33 ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ ተቋማት የአደጋ ደህንነት መስፈርትን እንዲያሟሉ የማስተማር፣ የመከታተልና የመቆጣጠር ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በዚህም በተለያዩ ሆቴሎች፣ የገበያ ማዕከላት ፣ድርጅቶች፣ ኢንዱስትሪዎች እና ሌሎች ተቋማት ላይ በተደረገው የፍተሻ ሥራ የአደጋ ደህንነት መስፈርትን አሟልተው የተገኙት 33ቱ ብቻ መሆናቸው አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኘነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት ማረጋገጫው ተቋማት እንደ ሕንጻቸው ሁኔታ፣ እንደሚሰጡት አገልግሎትና ያላቸዉን የሰዉ ሀይል መሰረት አድርጎ ማሟላት የሚገባቸው 26 የሚደርሱ ዓለም አቀፍ የደህንነት መስፈርቶችን ያካተተ ነዉ ብለዋል።

የእሳት ማጥፊያ መሳሪያ፣ የእሳት አደጋ ከመከሰቱ በፊት የሚያሳወቁ መሳሪያዎች፣ የአደጋ ጊዜ መውጫ፣ በአደጋ መቆጣጠር የሰለጠነ ባለሙያ፣ እሳትን ሊቋቋሙ ከሚችሉ ግብዓቶች የተገነባ ፣በአደጋ ጊዜ መሰብሰቢያ ስፍራ ከመስፈርቶቹ መካከል እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።

ሄኖክ ወ/ገብርኤል

ሚያዚያ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply