You are currently viewing በአዲስ አበባ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ የመንግስት የጸጥታ አካላት በህፃናት እና አረጋውያን ላይ ጭምር በወሰዱት ያልተመጣጠነ እርምጃ በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው ቢያንስ…

በአዲስ አበባ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ የመንግስት የጸጥታ አካላት በህፃናት እና አረጋውያን ላይ ጭምር በወሰዱት ያልተመጣጠነ እርምጃ በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው ቢያንስ…

በአዲስ አበባ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ የመንግስት የጸጥታ አካላት በህፃናት እና አረጋውያን ላይ ጭምር በወሰዱት ያልተመጣጠነ እርምጃ በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው ቢያንስ አንድ ሰው ሞቷል ሲል ኢሰመኮ አረጋገጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ የፀጥታ ኃይሎች ያልተመጣጠነ እርምጃ ወስደዋል ሲል ገልጧል። በወሰዱት እርምጃም ቢያንስ አንድ ሰው መገደሉን ማረጋገጡንና እርምጃውም በህፃናት እና አረጋውያን ላይ ጭምር የተወሰደ በመሆኑ በርካታ ሰዎች ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል ብሏል። ይህን የወንጀል ድርጊት የፈጸሙ የጸጥታ አካላትም ተለይተው እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል። በቀጣይ ጊዜያት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈፀም የፀጥታ ኃይሎች ተገቢውን ስልጠና እንዲሰጣቸውም አሳስቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply