በአዲስ አበባ የከተማ ፅዳት አጠባበቅ አሳሳቢ የሚባል ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ፡፡

በጤና ሚኒስቴር የንፅህና አጠባበቅ ቡድን መሪ አቶ አብርሃም ምስጋናው ለአሐዱ እንደገለፁት በሀገር አቀፍ ደረጃም ይሁን በአዲስ አበባ የንፅህና አጠባበቁ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡በተለይም ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ ለንፅህና መጠበቂያ የሚያገለግሉ መፀዳጃ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ባለመግባታቸው ከተሞች ውብና ፅዱ ለመሆን አስቸጋሪ እንዳደረገው ቡድን መሪው ገልፀዋል፡፡ችግሩ ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው በርካቶች በተገቢው መልኩ ቆሻሾችን ባለማስወገዳቸው ምክንያት ነው የሚሉት ቡድን መሪው ይህም ዜጎችን ለከፋ የጤና ችግር እያጋለጠ ነው ብለዋል፡፡

*******************************************************************************

ቀን 08/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply