
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ተማሪዎች በማንነታቸው ተመርጠው እየታፈኑ ነው ተባለ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 3/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ተማሪ እዘዝ ሞላ ተሻለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ አመት የህዝብ አስተዳደሪ ልማት ተማሪ ሲሆን ምንም ባላወቅነው ነገር ከቤተ ክርስቲያን ሲመለስ ማንነታቸው ባልታወቁ ሲቪል ለባሾች ግንቦት 3/2015 ከምሽቱ 12:15 ሰዓት ተወስዷል ሲሉ ጓደኞቹ ተናግረዋል። እኛ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምንማር የአማራ ተማሪወች ለመማር ተቸግረናል ብለዋል ሲል አሻራ ሚዲያ ዘግቧል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተወስዶ ከ3 ሳምንት በላይ በእስር ላይ የሚገኘው የ3ተኛ ዓመት የህግ ተማሪ ጆን ተሻገርም ሁከት ብጥብጥ ማነሳሳት ለተባለው የ6 ሽህ ብር ዋስትና ሲፈቀድለት እንደገና በሽብር ወንጀል ተጠርጥረሃል በሚል በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መቅረቡ ይታወቃል።
Source: Link to the Post