በአዲስ አበባ ያልተፈቀደ አገልገሎት ሲሰጡ በተገኙ 125 ማሳጅ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ ባለፉት ስድስት ወራት በመዲናዋ ከተቀመጠው የአገልግሎት ደረጃ ዉጪ አገልግሎት ሲሰጡ በተገኙ 125…

በአዲስ አበባ ያልተፈቀደ አገልገሎት ሲሰጡ በተገኙ 125 ማሳጅ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ባለፉት ስድስት ወራት በመዲናዋ ከተቀመጠው የአገልግሎት ደረጃ ዉጪ አገልግሎት ሲሰጡ በተገኙ 125 ማሳጅ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የማሳጅ ቤቶችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ተሬሳ እንደተናገሩት፤ ማሳጅ ቤቶች ለማህበረሰቡ መጤ ባህል ከማውረስ ባሻገር አምራቹን ዜጋ ወዳልተፈለገ መንገድ እንዲገባ እያደረጉ ናቸው።

በማሳጅ ቤቶች ላይ የሚደረገው የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ እደሚቀጥል ገልጸዋል።

በባለስልጣኑ የምግብና ጤንነት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ሚሬሳ ሚዴቅሳ በወቅቱ እንደገለጹት ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ161 ማሳጅ ቤቶች ላይ ቁጥጥርና የክትትል ስራ ተሰርቷል።

በቁጥጥር ስራው 125 ማሳጅ ቤቶች ከተቀመጠው የአገልግሎት ደረጃ ዉጪ አገልግሎት ሲሰጡ የተገኙ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 76 የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሁም 49 ማሳጅ ቤቶች እንዲታሸጉ ተደርጓል ብለዋል።(ኢ.ፕ.ድ)

የካቲት 07 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply