You are currently viewing በአዲስ አበባ ጋርመንት በተባለው አካባቢ የሚገኙ የባጃጅ አሽከርካሪዎች በማንነታችን ምክንያት በመንግስት የፀጥታ ሐይሎች ጥቃት እየደረሰብን ነው ሲሉ ወቀሱ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በአዲስ አበባ ጋርመንት በተባለው አካባቢ የሚገኙ የባጃጅ አሽከርካሪዎች በማንነታችን ምክንያት በመንግስት የፀጥታ ሐይሎች ጥቃት እየደረሰብን ነው ሲሉ ወቀሱ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በአዲስ አበባ ጋርመንት በተባለው አካባቢ የሚገኙ የባጃጅ አሽከርካሪዎች በማንነታችን ምክንያት በመንግስት የፀጥታ ሐይሎች ጥቃት እየደረሰብን ነው ሲሉ ወቀሱ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከየካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ጋርመንት አካባቢ ‹‹ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎችና በባጃጅ አሽከርካሪዎች መካከል ውጥረት መንገሱን ›› ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል፡፡ ቁጥራቸው ከሃያ የሚሻገር ቅሬታ አቅራቢዎች አሻም ስቱዲዮ አቤቱታቸውን ለማሰማት ማልደው መጥተዋል፡፡ ‹‹ ስማችን፣ አካላዊ ገፅታችን ለደህንነታችን ሲባል በካሜራ ዕይታ ውስጥ አይግባ›› ሲሉ የጠየቁት አሽከርካሪዎቹ ‹‹ በማንነታቸው ምክንያት ከስራ ገበታቸው እየተፈናቀሉ መሆኑን›› አስረድተዋል፡፡ ‹‹ በስፍራው ከ11 ዓመታት በላይ ሰርተንበታል፤ ወልደን ከብደንበታል፡፡›› የሚሉት አሽከርካሪዎቹ ‹‹ አሁን ግን የምንተዳደርበት ባጃጅ በፀጥታ ሐይሎች እየተወሰደብን ነው፤ በላያችን ላይም ሌላ ማህበር እየተደራጀ ነው፡፡›› ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ‹‹ የመንግስት የፀጥታ ሐይሎች በተወሠደው የሐይል እርምጃ ጉዳት የደረሰባቸው›› አሽከርካረዎችም ደርሶብናል ያሉትን በደል ገልፀዋል፡፡ ከእነርሱ መካከል ‹‹ በሐይል እርምጃው አንደኛው በሰደፍ፣ አንደኛ ደግሞ በጥይት ጉዳት እንደደረሰባቸው›› ተናግረዋል፡፡ አሻም ሚዲያ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply