You are currently viewing በአዲስ አበባ ጋርመንት አካባቢ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ_ባጃጆች በአካቢው እንዳያሽከረክሩ ክልከላ ተደረገ፤ ክልከላውን በሰላማዊ ሰልፍ ባወገዙ ወጣቶች ላይ ፖሊስ ጥይት በመተኮሱ የቆሰሉ አ…

በአዲስ አበባ ጋርመንት አካባቢ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ_ባጃጆች በአካቢው እንዳያሽከረክሩ ክልከላ ተደረገ፤ ክልከላውን በሰላማዊ ሰልፍ ባወገዙ ወጣቶች ላይ ፖሊስ ጥይት በመተኮሱ የቆሰሉ አ…

በአዲስ አበባ ጋርመንት አካባቢ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ_ባጃጆች በአካቢው እንዳያሽከረክሩ ክልከላ ተደረገ፤ ክልከላውን በሰላማዊ ሰልፍ ባወገዙ ወጣቶች ላይ ፖሊስ ጥይት በመተኮሱ የቆሰሉ አሉ፤ በርካቶቸችም ለእስር እና ለድብደባ ተዳርገዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጋርመንት አካባቢ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ_ባጃጆች በአስፓልት ላይ እንዳያሽከረክሩ የተደረገው ክልከል በሰላማዊ ሰልፍ ተወግዟል። የአዲስ አበባ ፖሊስ እና አድማ በታኞች ጥይት በመተኮሳቸው የቆሰሉ እንዳሉ እንዲሁም በርካቶቸች ለእስር እና ለድብደባ መዳረጋቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 14 እና ወረዳ 15 ከ01 የተቀነሰ፣ በላፍቶ ወረዳ 11፣ ወረዳ 01 በአጠቃላይ ጋርመንት አካባቢ ባጃጅ ማሽከርከር መከልከሉ ተገልጧል። ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ቅሬታቸውን የገለጹ አሽከርካሪዎች እንዳሉት የካቲት 28/2015 ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የባለ ሶስት እግር የባጃጅ አሽርካሪዎች “እንዳንሰራ ልንከለከል አይገባንም፣ ምን ሰርተን እንብላ፣ የት እንሂድ!” በሚል ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ባጃጆቻቸውን በሙሉ መንገድ ላይ በማቆም ለችግራቸው መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ይሁን እንጅ ነዋሪዎች እንደገለጹት የአዲስ አበባ ፖሊስ እና አድማ በታኞች፣ በጋራ ሆነው በወሰዱት እርምጃ 2 ባለባጃጆች ቆስለዋል፣ ከ20 በላይ በግራር ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል፣ በላፍቶ አካባቢ ደግሞ ከ20 በላይ ታስረዋል በድምሩ ቢያንስ ከ40 በላይ ባለ ባጃጆችና መንገደኞች ጭምር ታፍሰው ታስረዋል። አዲስ ቢያድጌ እና ጓደኞቹ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ማህበር ብቻ ከ10 በላይ ሾፌሮች በግራር ፖሊስ ጣቢያ በጅምላ ታስረውበታል። እንደአብነትም ከማህበሩ አባላት መካከል መካሽ መስፍን፣ ከበደ ተስፋዬ፣ አይተነው፣ አዱኛ፣ ግርማ እና ሌሎችም ይገኙበታል። በግምት ከ200 በላይ የሚሆኑ ባጃጆች በ3 ክሬን ወደ ቦሌ አቅጣጫ እየተጫኑ ተወስደዋል ሲሉም አክለዋል። የካቲት 27/2015 ትራፊክ ፖሊስ በፓትሮል እየዞረ በሞንታርቦ “ሶስት እግር ባጃጅ ከየካቲት 28/2015 ጀምሮ አስፓልት ላይ እንዳይሰሩ መከልከሉን ምንጮች አውስተዋል። በዚህም:_ 1) ከጆሞ ወደ መብራት ኃይል፣ 2) ከላፍቶ ወደ ሙዚቃ ቤት፣ 3) ከመብራት ወደ ኃይሌ ጋርመንት፣ 4) ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ሰፈራ፣ 5) ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ሀና ማርያም፣ 6) ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ጋራ በአዲሱ መንገድ፣(ሀጫሉ መንገድ) ያሉ መስመሮች ሁሉ ለባለ ባጃጅ አሽከርካሪዎች ዝግ በመደረጋቸው መቸገራቸውን የገለጹት ምንጮች አካሄዱ ኢፍትሃዊ እና አምባገነናዊ ነው ብለውታል። ይህ ውሳኔ በመንገድ ትራንስፖርትና ትራፊክ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ የተወሰደ ነው ሲሉም አክለዋል። ከ3 ወር በፊት ጀምሮ ባጃጅ ማለፍ አይችልም በሚል ተከልክሏል ቢባልም በመካከላቸው ስምምነት ስላልነበረ እስካሁን ተፈጻሚ አልነበረም ተብሏል። ሌላኛው አስተያየት ሰጭ እንደሚለው ይህ ባጃጆችን ከስራ የማስቆም ተግባር የተፈጸመው ጥናት አድርጎ ማንነትን ከለዩ በኋላ ነው፤ ይህም ከ95% በላይ አሽከርካሪዎች አማራ መሆናችነፈ ካረጋገጡ በኋላ የወሰዱት የታቀደ እርምጃ ነው ሲል አውግዞታል። በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የዜጎች ቤት የፈረሰውም ጥናት ከተደረገ በኋላ አማራውን ለማዳከም እና ከአዲስ አበባ ለማስወጣት እንደሆነው ሁሉ ቀደም ሲል ባለባጃጆችንም ሰብስበው:_ 1) የመግዣ ገንዘቡን መከላከያ ገድላችሁ ያገኛችሁትን ክላሽ ሽጣችሁ ነው የገዛችሁት፣ 2) እናንተ ፋኖዎች ናችሁ በማለት ሲያስፈራሩ እንደነበር ገልጸዋል። በመጨረሻም የሚመለከተው አካል ለገጠማቸው ችግር አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የተወሰደውን እርምጃ የሚያሳይ ሙሉ ቪዲዮ ከስር አያይዘናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply