በአዲስ አበባ 1.5 ሚሊዮን የቤት እጥረት መኖሩ ተነገረ።አልሚዎች በየአመቱ 200 እና ከዚያ በላይ ቤቶች እየገነቡ የከተማዋ የቤት ችግር መቅረፍ አይቻልም ተብሏል።በመሆኑም ባለሀብቶች በቤት…

በአዲስ አበባ 1.5 ሚሊዮን የቤት እጥረት መኖሩ ተነገረ።

አልሚዎች በየአመቱ 200 እና ከዚያ በላይ ቤቶች እየገነቡ የከተማዋ የቤት ችግር መቅረፍ አይቻልም ተብሏል።

በመሆኑም ባለሀብቶች በቤት ልማት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ የከተማ አስተዳደሩ ጠይቋል።

በቤት ልማት መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ከተማ አስተዳደሩ ማበረታቻ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ግርማ ሰይፊ እንደተናገሩት በከተማው ያለው የቤት ፍላጎት እና አቅርቦቱ የተመጣጠነ አይደለም ብለዋል።

ከተማዋ በልማት ምክንያት በርካታ ቤቶች በልማት እያፈረሰች ከመሆኑ ጋር በተያያዘም የቤት ፍላጎቱ እየጨመረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ከፍተኛ ፍላጎት የሚታይበት የቤት ችግር ለመቅረፍ ከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ አማራጮች እያቀረበ ይገኛልም ብለዋል።

የሪልዕስቴት አልሚዎች በአመት 200 እና ከዚያ በላይ ቤት እየሰሩ የከተማው የቤት ፍላጎት ማሟላት አይቻልም ሲሉም ተናግረዋል።

ባለሀብቶች ከሪል ዕስቴት ከፍ ብለው በቤት ልማት ውስጥ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

ከዚህ በፊት በዘርፉ የነበሩ ማነቆዎች ከተማ አስተዳደሩ እየቀረፈ እንደሚገኝ የተናገሩት ኮሚሽነር ግርማ ባለሀብቶች ዕድሉን መጠቀም አለባቸው ብለዋል።

ኮሚሽነሩ ይህንን ያሉት በቤት ልማት ዘርፍ ላይ የተሰማራው ዋልያ ሆምስ ባዘጋጀው መድረክ ነው።

ዋልያ ሆምስ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የገነባቸው ቤቶች በተመለከተ የማስተዋወቂያ ዝግጅት አድርጓል።

ኩባኒያው ኡቡንቱ ዴሉክስ አፓርትመንት እና አጃንባ ቪላስ የተሰኙ ሁለት ፕሮጀክቶቹ ለዘርፉ ተዋናዮች እና ለመንግስት ሀላፊዎች አስተዋዉቋል።

የዋልያ ሆምስ አፓርትመንቶች የሚገኙት በላንቻና በቅሎ ቤት አካባቢ መሆኑ ተነግሯል።

ሄኖክ ወ/ገብርኤል
ሚያዚያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply