በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ በተለምዶ አደሬ ሰፈር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ቤቶች ተቃጥለዋል።አደጋው የደረሰው ዛሬ እ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/CQr_iDOEbd4zkWyIavoG86bRp3fmX7F-HYgYglaC8O6S8Zr2mXKRn7yxo5mhuDlIKcjyVXzI1gj9GzPpIjC7piFtPPvC8bHPuVgHMt7yD0qeBWgpkJ3mmTQGDGHlWG3xctdk7E6eGSMBsl_IhC2rYE8JozRui8LllAbN9Cv2-atXH0mj0hz3xx7PjiWUbJQVPHvzp--klKd8tnJ13VmE9NMcf639mVBbSr63pxXUcmXq67wxhl5HI4yRgvfSuxLXsoQGLwzBS_ShTH4AcgQJceD5IDpTetjXYniLUY2pLKTmC1Sa_qpncCRav0wwNu5Mzrx7266ayOI0mC_aRYvKSg.jpg

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ በተለምዶ አደሬ ሰፈር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ቤቶች ተቃጥለዋል።

አደጋው የደረሰው ዛሬ እሮብ ከቀኑ 8:45 ላይ ነው፡፡

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 9 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ከ51 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማሩ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ ፈጥነዉ በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል።

አደጋዉ የአጋጠመበት ስፍራ የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን የማያስገባና የተጠጋጉና ለአደጋ የተጋለጡ የመኖሪያና የንግድ ቦታ ነዉ።

በእሳት አደጋዉ በአንድ ሰዉ ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።
የተቃጠሉት 8 የንግድና የመኖሪያ ቤቶች ናቸዉ፡፡

የእሳት አደጋው መንስኤ እንዲሁም ያስከተለው የጉዳት መጠን በቀጣይ ተጣርቶ ይገለፃል ተብሏል፡፡

@የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን

Source: Link to the Post

Leave a Reply