በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ሰዎችን በማገትና በተያያዥ ወንጀሎች የተከሰሱ 6 ግለሰቦች የቅጣት ውሳኔ ተሰጣቸው።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ…

በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ሰዎችን በማገትና በተያያዥ ወንጀሎች የተከሰሱ 6 ግለሰቦች የቅጣት ውሳኔ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ…

በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ሰዎችን በማገትና በተያያዥ ወንጀሎች የተከሰሱ 6 ግለሰቦች የቅጣት ውሳኔ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምእራብ ጎንደር ዞን በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ የሰው እገታ ወንጀል በፈፀሙ በ6 ግለሰቦች ላይ የእስራት ውሳኔ መሰጠቱን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል። የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አሻግሬ አስረስ እንደተናገሩት በወረዳችን ባሉ ቀበሌዎች ከሃምሌ 13/2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 15 /2013 ዓ.ም ድረስ ህዝባችን በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዳይገባ ሲያውኩ የነበሩ፣ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ በርካታ ፀረ-ሰላም ሐይሎች በተደረገው የጥምር ኮሚቴ ኦፕሬሽን በህግ ፊት ሊቀርቡ ችለዋል ብለዋል። በተለይ በወረዳው በርካታ የፀረ- ሽብር ጥምር በመፍጠር ሰዎችን እያገቱ ለእያንዳንዳቸው ከ150 ሺህ ብር እስከ ከ300 ሺህ ብር በመጠየቅ የአካባቢውን ማህበረሰብ ሲያውኩ እንደነበር ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል። ኢንስፔክተሩ አሁን ላይ በተደረገው የጥብቅ ዲሲፒሊን ኦፕሬሽን 9 ግለሰቦች በወንጀል ተጠርጥርው መያዝ መቻላቸውን ጠቅሰዋል። ዋና ኢንስፔክተር አሻግሬ አስረስ እንደተናገሩት በሰው ማገት ወንጀል ከተያዙት ዘጠኝ ግለሰቦች መካከል የሚመለከተው አካል ምርመራ በማድረግ በስድስቱ ላይ ከ4 ዓመት እስከ 24 ዓመት የፍርድ ቅጣት መስጠቱንና በ3ቱ ግለሰቦች ላይ ደግሞ የህግ ክትትልና ምርምራ እየተደረገ በመሆኑን በቀጣይ ውሳኔ ሲሰጥ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ማህበረሰባችንና የፀጥታ አካሉ በቅንጅት በመስራት ወንጀለኞች እንዲያዙ ላደረገው አስተዋፅኦ አመስግነው ይህ ተግባር በመስራቱ ህዝባችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ደስታን የፈጠረና በወረዳችን ላይ የተሻለ ሰላም እየመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በሰው ማገት እና በሌሎች ወንጀል ተጠርጥረው የእስራት ውሳኔ የተሰጣቸው ስም ዝርዝር:_ 1ኛ. ውቤ አለነ 24 አመት 2ኛ . የሻባ ጤናው 12 አመት 3 ኛ. ሰጤ ማለድ 8 አመት ከአምስት ወር 4ኛ. ላቀው አቤልነህ 7 አመት ከስምንት ወር 5ኛ. ፍቃዱ ምህረት 6 አመት ከ3 ወር 6ኛ. ማሙሽ አግተው 4 አመት ከአምስት ወር ምንጭ_የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን

Source: Link to the Post

Leave a Reply