You are currently viewing በአዴት ከተማ አስተዳደር ውስጥ የመኖሪያ ቤት ለማግኘት ተደራጅተው በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች የወረፋ መዛባት እየተፈጠረ ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲ…

በአዴት ከተማ አስተዳደር ውስጥ የመኖሪያ ቤት ለማግኘት ተደራጅተው በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች የወረፋ መዛባት እየተፈጠረ ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲ…

በአዴት ከተማ አስተዳደር ውስጥ የመኖሪያ ቤት ለማግኘት ተደራጅተው በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች የወረፋ መዛባት እየተፈጠረ ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 20 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ጎጃም ዞን አንዴት ከተማ አስተዳደር ከ2007 ጀምረው ሂደቱን እያሟሉ የቆዩ ከ200 በላይ ማህበራት ቅሬታ አቅርበዋል። ቅሬታው የቀረበው ለአዴት ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ለከተማ አገልግሎት እና ለሌሎችም ተቋማት ከ2007 ጀምረን የከተማ ቦታ ለማግኘት ተደራጅተን ወረፋ በመጠባበቅ ላይ የቆዬን የካቲት 13/2015 በ2007 ዓ/ም ጀምሮ በመመሪያው መሰረት 24 ሀያ አራት በመሆን የመኖሪያ ቦታ ለማግኘት የተደራጀን የአዴት ከተማ ነዋሪዎች እስካሁን ድረስ ከአሰራር ውጭ በመሆን በተንዛዛ ቀጠሮ አይደለም መሬት፣ እውቅና እንኳ ለመስጠት አልቻሉም ሲሉ ወቅሰዋል። በ2011 የተደራጁ የብሎኬት ማህበር እውቅና ይሰጣቸው ተብሎ ሲጻፍላቸው ለእኛ ከ2007 ጀምረን ወረፋ የተያዘልን አካላት እስካሁን ስለምን እውቅና አልተሰጠንም ያሉ ከ110 በላይ ቅሬታ አቅራቢዎች ወደ አማራ ክልል ህብረት ስራ ማህበራት መምሪያ ማቅናታቸውን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ገልጸዋል። በአዴት ከተማ አስተዳደር ውስጥ የመኖሪያ ቤት ለማግኘት ተደራጅተው በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች የወረፋ መዛባት እየተፈጠረ ነው ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል። አካሄዱ ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ እና ፍትሃዊነት የጎደለው ነው በማለት የካቲት 20/2015 ከጠዋት ጀምረው ለአቤቱታ ወደ ባህር ዳር አቅንተዋል። በእለቱም ለአማራ ክልል ህብረት ስራ ማህበራት መምሪያ አስቸኳይ ማስተካከያ እንዲደረግ የሚጠይቅ አቤቱታ አስገብተዋል። ቅሬታ የቀረበለት መምሪያውም ለጊዜው እገዳ መጣሉን በደብዳቤው አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply