You are currently viewing በአድዋ መንፈስ የአማራነት ክብራችንን እናስመልሳለን‼️ ** የአድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች አብረቅራቂ ድል፣ የኢትዮጵያዊያን አይበገሬነት የማይደበዝዝ ምልክት ከመሆኑ ባሻገር ዓለማቀፍ  የእሳቤ…

በአድዋ መንፈስ የአማራነት ክብራችንን እናስመልሳለን‼️ ** የአድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች አብረቅራቂ ድል፣ የኢትዮጵያዊያን አይበገሬነት የማይደበዝዝ ምልክት ከመሆኑ ባሻገር ዓለማቀፍ የእሳቤ…

በአድዋ መንፈስ የአማራነት ክብራችንን እናስመልሳለን‼️ ** የአድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች አብረቅራቂ ድል፣ የኢትዮጵያዊያን አይበገሬነት የማይደበዝዝ ምልክት ከመሆኑ ባሻገር ዓለማቀፍ የእሳቤ ፈለግን የቀየረ፣በማይደገም ሁኔታ የተፈፀመ ክስተት ነው፡፡ የአደዋ ድል ፋይዳ ከኢትዮጵያ ድንበር ይሻገራል፤ ከአፍሪካ ማዕቀፍም ያልፋል፡፡ አድዋ ፋሽዝምን አሸንፎ ብቻ አልተወውም ፡፡ ይልቁንም የበቀለበትን አፈር አድርቆ ሁለተኛ የፋሽዝም ዘር እንዳይበቅልበት አኮላሸው፡፡ ፋሽዝም የበቀለው “ሶሻል ዳርዊኒዝም” በሚባል የእበልጣለሁ ባይነት ፣የአውዳሚነት፣የዘረኝነት እና የጭካኔ አፈር ላይ ነው፡፡ ሶሻል ዳርዊኒዝም የዳርዊንን “የበለጠ ብርቱ የሆኑ ፍጥረታት ብቻ ህልው ሆነው ይኖራሉ”(The fittest will survive) የሚለውን የሥነ-ፍጥረታዊ የምርም ግኝ…ነት በቀጥታ ወደ ማህበራዊው ሳይንስ አውድ አምጥቶ ገቢራዊ ለማድረግ የተሞከረበት የጥፋት ስንቅ ነው፡፡ በሶሻል ዳርዊኒዝም እሳቤ የበለጠ ብርቱ የተባለው ነጭ ቆዳ ያለው የሰው ፍጡር አዋቂ፣ይገዛ ይነዳ ዘንድ የተገባ ሲሆን በተቃራኒው ጥቁር ሆኖ የተወለደው ብርቱ ያልሆነ፣ በአዋቂው ነጭ ፍጡር ይገዛ ይነዳ ዘንድ ድኩም አፈጣጠሩ የሚያስገድደው ነው ተብሎ ይታሰባል ፡፡ ይህ እሳቤ ነው የበርሊን ጉባኤን” The Berlin conference” የወለደው፡፡ በዚህ ጉባኤ አፍሪካ እንደ ቅርጫ ስጋ ተከፋፍላ “አዋቂ” እና “ብርቱ” ለተባለው ነጭ ወራሪ ተላልፋ ተሰጠች፡፡ መላው አፍሪካ በነጭ ወራሪ እጅ ወደቀ፡፡ ይህም ለሶሻል ዳርዊኒዝም ህግ “ትክክለኝነት” ማስረጃ ሆኖ ቀረበ! ስለ ትክክለኛነቱ ብዙ ማስረጃ የቀረበበትን የሶሻል ዳርዊኒዝም ህግ ታፈርስ ዘንድ አድዋ በእምየ ምኒልክ አእምሮ ተፃፈች፣በእቴጌ ጣይቱ ብልሃት ተደወረች፡፡ አድዋ መፍረስ የሚገባውን አፍርሳ ዓለም ይሽከረከርበት የነበረውን የዘረኝነት ምህዋር ቀየረች፤እኩልነትን በደም ፃፈች፤ የአሸናፊና የተሸናፊን ቦታ ቀየረች፤የፈጣሪዎቿን የእምየ ምኒልክን/የእቴጌ ጣይቱን ስም በማይጠፋ ቀለም ፃፈች፤ የኢትዮጵያዊያንን አይበገሬነት ለዓለም አወጀች፡፡ አድዋ ላይ የተከናወነው ባይከናወን ኖሮ ሶሻል ዳርዊኒዝም የአዓለማችን ገዥ ሃሳብ ሆኖ ይዘልቅ ነበር፡፡ ግን አልሆነም! ይህ ይፈፀም ዘንድ ምኒልክነትን ይጠይቅ ነበር፣ ጣይቱነትን ይሻ ነበር፡፡ ምኒልክነት የማይሆን የተባለን ይሆናል ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ምኒልክነት ዝቅ አድርጎ በሚያይ ዘረኛ መቃብር ላይ ከፍ ብሎ መከሰት ነው፡፡ ምኒልክነት የማይቻለውን መቻል ነው፡፡ምኒልክነት ሁሌ የሚደምቅ አለመረሳት ነው፡፡ ምኒልክነት ሞቶ መኖር ነው፡፡ ምኒልክነት ገራገርነት እና እሳትነት በአንድነት ሲኖሩ ማለት ነው፡፡ ምኒልክነት ማስፈራት ነው፡፡ ምኒልክነት ሃገር የማቆም ብልሃት ነው፡፡ ምኒልክነት ግዝፈት ነው፡፡ ምኒልክነት በወኔ ጀምሮ በብልሃት መጨረስ ነው፡፡ ምኒልክነት መከናወን ነው፡፡ ምኒልክነት ሰርቶ ማሰራት ነው፡፡ ምኒልክነት መነሻና መድረሻን ጠንቅቆ ማወቅ ነው፡፡ ምኒልክነት ሃገር ማቆየት ነው፡፡ ምኒልክነት የሚደመጥን ማድመጥ ነው፡፡ ጣይቱን ለማድመጥ ምኒልክነትን ይጠይቃል፤በምኒልክ ለመደመጥም ጣይቱነትን ይሻል! ምኒልክነት የማይሆን የተባለን ይሆናል ብሎ ማሰብ ነው ።ምኒልክነት ዝቅ አድርጎ በሚያይ ዘረኛ መቃብር ላይ ከፍ ብሎ መከሰት ነው ።ምኒልክነት የማይቻለውን መቻል ነው ።ምኒልክነት ሁሌ የሚደምቅ አለመረሳት ነው ።ምኒልክነት ሞቶ መኖር ነው ።ምኒልክነት ገራገርነት እና እሳትነት በአንድነት ሲኖሩ ማለት ነው ።ምኒልክነት ማስፈራት ነው ።ምኒልክነት ሃገር የማቆም ብልሃት ነው ።ምኒልክነት ግዝፈት ነው ።ምኒልክነት በወኔ ጀምሮ በብልሃት መጨረስ ነው ።ምኒልክነት መከናወን ነው ።ምኒልክነት ሰርቶ ማሰራት ነው ።ምኒልክነት መነሻና መድረሻን ጠንቅቆ ማወቅ ነው ።ምኒልክነት የሚደመጥን ማድመጥ ነው ።ጣይቱን ለማድመጥ ምኒልክነትን ይጠይቃል፤በምኒልክ ለመደመጥ ጣይቱነት ይሻል!! ምኒልክነት ጣይቱን ዘውድ አድርጎ እነ ሃብቴ አባ መላን አስከትሎ አድዋን ገቢራዊ አደረገ ።አድዋ የፋሽስቱን ሃገር ጣሊያንን ጭምር በግድ “ቪቫ ምኒልክ” ያስባለች ትንግርት ነች! አድዋ የቅዠት ትርክት የማያደበዝዘው የምኒልክ እጅ ስራ ነች ። የአባቶቻችንን እጅ ሰርቶ ያሳየን የድል እንጂ የሽንፈት ፅዋ አይደለም ።የአድዋ ልጆች ነን ስንል ከድል ነሽ ወገን ነን ለማለት ነው ።አድዋ ድል የተነሳችው የዘመኗን ዘረኝነት ነው ።እኛም የአድዋ ልጆች ነን ለማለት የምንበቃው ወገኖቻችንን በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ እየተለዩ የሚያሳድደውን የዘመናችንን የዘረኝነት ፍላፃ ድል መንሳት ስንችል ነው ።ይህ ገቢራዊ ሳናደርግ ከአድዋ መንፈስ የተወለድን የአባቶቻችን ልጆች ነን ማለት አንችልም ።እየተሳደዱ ፣እየሸሹ ፣ክብረ-ቢስ ሞት እየሞቱ ፣አንገት እየደፉ የአድዋ ልጅነት የለም ፤በሽንፈት ውስጥ ሆኖ የአድዋ መንፈስ መሆን አይቻልም ። በአሁኑ ወቅት እንደ አማራ ወጣት/ህዝብ ያለንበት ሁኔታ ከአድዋ መንፈስ ተጋሪ ለመሆን ብቁ ያደርገናል ወይ? ብሎ ራስን መጠየቅ ያስፈልጋል ።የአማራ ህዝብ አሁን ያለበት የመሳደድ ፣የመዋረድ ፣አንገት የመድፋትና የመታደን ሁኔታ የአድዋ መንፈስ ነፀብራቅ አይደለም ።የአድዋ መንፈስ ታዳሚ ለመሆን ይህ ታሪክ መቀየር አለበት ።ይህ ታሪክ ባልተቀየረበት ሁኔታ አድዋ ማክበር ግንጥል ጌጥ ነው ፤የእሳት ልጅ አመድ መሆን ነው! የእሳት ልጅ አመድ አባቱን ይመስል ዘንድ ከነክብሩ ማስፈራቱ መኖር አለበት ።የመጣው ሁሉ ክብሩን የሚነካው ፣የመኖር እጣፈንታው በዘረኞች በጎ ፈቃድ እጅ የወደቀው ፤ሰብአዊ ክብሩን የተነጠቀው ፣በሃገሩ ላይ የመዘዋወር መብቱ ድርድር ውስጥ የገባው የዚህ ዘመን የአማራ ትውልድ ከአድዋ መንፈስ ጋር ያለውን መስተጋብር ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል ። የአማራ ህዝብ የሃገረ መንግስትን ምንነት ጠንቅቆ የሚያውቅ ፣በነኩት ቁጥር የማይበረግግ ጠንካራ ስነልቦና ያለው ህዝብ ነው ።ሃገርን ያተረፈ መስሎት የማይቻለውን ችሎ ፣የማይታገሱትን ታግሶ ኖሯል ።ሆኖም ሁሉም ድንበር ወሰን አለው ።ሁሉም ነገር በቃ የሚባልበት ፣ፅዋ የሚሞላበት ወቅት አለ ።ክብርን አሳልፎ በመሰጠት የሚገለፅ አስተዋይነት የለም ።ስለሆነም የአማራ ህዝብ ትግስት ጠላት ብለው በሚያሳድዱት የቁማር ፓለቲከኞች የተተረጎመበትን መንገድ አጢኖ ፣ትግስቱ ከፍርሃት መቆጠሩን ደምድሞ ፣የለም ያስባለውን ዝምታውን በቃ ብሎ ከአባቶቹ የወረሰውን የተጋፋጭነት ስነልቦና አንግቦ የተጋረጠበትን የህልውና ስጋት ለመጋፈጥ ከዳር እስከ ዳር መነሳት አለበት ። በውርደት ላይ መተኛት የአማራነት እሴት አይደለም! ስለሆነም የተዳፈነ የመሰለውን ክብርን በክንድ ማስመለስ የአማራነት እሴት ፈልቅቀን አውጥተን ፣ሁለንተናዊ ክብራችንን የምናስመልስበት ፣መናቃችንን በማስፈራት የምንተካበት ወቅት ላይ ነን ።ይህን ነገ ዛሬ ሳንል ገቢራዊ ስናደርግ ብቻ ከአድዋ መንፈስ የተገኘን የአባቶቻችንን ልጆች መሆናችን እናስመሰክራለን ። አባቶቻችን ፋሽዝምን ብቻ ሳይሆን የበቀለበትን የሶሻል ዳርዊኒዝም አፈር እንዳመከኑት ሁሉ በዘመናችን የተጋረጠብንን የፀረ-አማራ ስርዓተ-መንግሰት አለት አንከባለን በላዩ ላይ በክብር እንገለጣለን!! ከአድዋ መንፈስ የወረስነውን ክብር በክንድ የማስመለስ ስራ የምንሰራበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ። 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል በዚህ መንፈስ ሆነን እናከብራለን ! ክብር ወድቀው ላቆሙን የአድዋጀግኖች ፤ዘላለማዊ ድርብ ድርብርብ ክብርና ሞገስ ለሚኒልክነት/ለጣይቱነት!! ክብር የአማራነትን ክብር ለማስመለስ ለወደቁ ፋኖ ወንድም እህቶች!! ህልውናችን በክንዳችን‼️ የካቲት 22/2015 ዓ.ም የአማራ ወጣቶች ማህበር

Source: Link to the Post

Leave a Reply