በአድዋ ድልድይ ስር የፈነዳው ፈንጂ፤ ፍተሻው በመጠንከሩ እጃቸው ላይ እንዳይገኝ የፈሩ የጣሉት እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 2 ቀን 2013…

በአድዋ ድልድይ ስር የፈነዳው ፈንጂ፤ ፍተሻው በመጠንከሩ እጃቸው ላይ እንዳይገኝ የፈሩ የጣሉት እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ስሙ አድዋ ድልድይ በሚባለው ቦታ ከጠዋቱ 2 ሰአት አካባቢ አንድ የታክሲ የረዳት ልጅ ለመፀዳዳት ወደ ድልድዩ ስር ገብቶ በነበረበት ወቅት በማዳበርያ ተጠቅልሎ የታሰረ ነገር አይቶ ምን ይሆን ብሎ ሲነካው እንደፈነዳ ተገልጧል፡፡ ልጁ ቀላል ጉዳት ደርሶበት ምኒሊክ ሆስፒታል እየታከመ ይገኛል ተብሏል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮማንደር ፋሲካ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ኮማንደር ፋሲካ የጸጥታ ሀይሉ ባጠቃላይ በጥምር ተደራጅቶ የቁጥጥር፣የፍተሻ እና ድንገተኛ የአሰሳ ስራ እየሰራ ነው ሲሉ የገለፁ ሲሆን የህዝቡ ጥቆማና የፀጥታ ሀይሉ ጠንካራ እንቅስቀሴ ያስጨነካቸውና ያስፈራቸው እጃቸው ላይ ጦር መሳርያ ያላቸው ሰዎች እየመጡ ከሚያስረክቡት ሌላ ፤ ውጪ እየጣሉ የሚገኙ አሉ ብለዋል፡፡ በተለይ በአቃቂ ቃሊቲ፣በቦሌ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣በኮልፌ ቀራኒዮ እና ወጣ ወጣ ባሉ አካባቢዎች ይሄ ተስተሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ እጁ ላይ ጦር መሳርያ ካለ እንዲያስረክብ ጥሪያቸውን ያቀረቡ ሲሆን አካባቢውን በጥንቃቄ መከታተሉን፣መጠቆሙን እና መሰል ቁሶችን በጥንቃቄ መመርመሩን እንዳይረሳ አሳስበዋል ሲል የዘገበው ኢትዮ መረጃ ኒውስ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply