‹‹በአገልግሎት ወቅት ለተፈጠሩ ቅሬታዎች ይቅርታ እንጠይቃለን››… ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ
–
በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ያሰናዳው የጳጉሜን አንድ ‹‹ የይቅርታ ቀን›› እየተከበረ ይገኛል፡፡
–
በዚህ ወቅት መልእክታቸውን ያስተላለፉት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ የጳጉሜን ወር በትርጓሜው የምህረት ወር ተብሎ እንደሚታወቅ አስታውሰው ዛሬ ላይ ስለ ቅርታና ምህረት ማውራት ተገቢ መሆኑን አንስተዋል፡
–
ይቅርታ የትላንትን ስህተት፤ በበደልና ቁርሾ በመተው ዛሬን በጥበብ ለመኖር የሚያስችለን መንገድ አንደመሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ የአገልግሎት ወቅት ለተፈጠሩ ቅሬታዎች የከተማዋን ነዋሪዎች ይቅርታ እንደሚጠይቁ ገልጸዋል፡፡
–
‹‹አዲስ አበባን እንደስሟ ውብና ማራኪ ለማድረግና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ የነዋሪዎቿን ድጋፍ እንፈልጋለን፤ ያለ ከተማዋ ነዋሪ አጋርነት ምንም መስራት አይቻልም›› በማለት ነው ያስረዱት፡፡
–
የታሪክ ምሁራን የቆየውን የኢትዮጵያውያንን የይቅርታ ባህል መልሰው እንዲያስተምሩ፣ ፖሊተከኞችም ከቂምና ጥላቻ ይልቅ ይቅርታን፤ አብሮነትንና አንድነትን እንዲሰብኩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
–
በበዓሉ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ፣ የሀይማኖት መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
–
ወርሀ መስከረምን በአዲስ ተስፋ ለመቀበልና ለፈጣሪ የምናቀርበው ልመና እንዲሰማ በይቅርታ የታደሰ ልብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
–
በበቀል የሰለለን አጥንት የሚያለመልመው ይቅርታ በኢትዮጵያውን ዘንድ በግጥም፤በንግግር፣ በጫወታ በሃል እንደሚነሳና የየእለት ሕይወት አካል መሆኑን ጠቅሰው የይቅርታ አድራጊ ልብ ለሌሎች ይተርፋል ነው ያሉት፡፡
–
አዲሱን አመት ከበቀልና ጥላቻ ስሜት ርቀን በተስፋ በመቀበል ኮቪድን የምናሸንፍበት እንዲሆን እመኛለው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
Source: Link to the Post