You are currently viewing በአገራችን 8 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች በጡት ካንሰር ይጠቃሉ።

በአገራችን 8 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች በጡት ካንሰር ይጠቃሉ።

በአለም ዓቀፍ ደረጃ በወንዶች ላይ የሚከሰት የጡት ካንሰር መጠን ከ1 በመቶ በታች ቢሆንም በአገራችን ግን 8 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።

በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በተደረገ ጥናት በወንዶች ላይ የሚከሰት የጡት ካንሰር መጠን በአጠቃላይ 8 በመቶ መሆኑ ነው የተገለፀው።

በአዳማ እና በጎንደር ከተሞችም ተመሳሳይ ጥናት መደረጉ የተገለፀ ሲሆን፣ ፤በጎንደር 13 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች በጡት ካንሰር ይጠቃሉ።

በአገራችን ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው በሴቶች ላይ የሚከሰት የጡት ካንሰር ቢሆንም በወንዶች ላይም የመከሰት እድል እንዳለው ተገልጿል።

እንደ አገር በሴቶች ላይ የሚከሰት የጡት ካንሰር 32 በመቶ የሚይዝ ሲሆን ፤ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ደግሞ በወጣቶች ላይ የሚከሰት ነው።

በጡት ካንሰር ተይዘው ወደ ህክምና ተቋማት ከሚመጡ ሰዎች መካከል ከ70-80 በመቶ የሚሆኑት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ የሚመጡ ናቸው።

በ2020 በተደረገ ጥናት በአለም ላይ በየአመቱ 2.2 ሚሊየን አዳዲስ ሴቶች በጡት ካንሰር ይያዛሉ።

የጡት ካንሰር እንደ ማህፀን በር ካንሰር ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ስለማይቻል ቀድሞ በመለየት እና ህክምና በመውሰድ መዳን የሚቻል ህመም ነው።

“የጡት ካንሰርን አስቀድሞ መለየትና ማከም ህይወትን ያድናል” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት ወሩን ሙሉ የሚታሰበው አለም አቀፉ የጡት ካንሰር ወር እየተከበረ ይገኛል።

በእስከዳር ግርማ እና ረድኤት ገበየሁ

መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply