በአገር ደረጃ አዲስ  የኮቪድ-19 ወጀብ መከሰቱን የኢትዮጵያ  ህብረተሰብ ኢኒስቲትዩት አስታወቀሰሞኑን የተከሰተውን  ጉንፋን  መሰል ወረርሽኝ  ተከትሎ በአንዳንድ ተቋማት  በተደረገ  ምርመራ…

በአገር ደረጃ አዲስ  የኮቪድ-19 ወጀብ መከሰቱን የኢትዮጵያ  ህብረተሰብ ኢኒስቲትዩት አስታወቀ

ሰሞኑን የተከሰተውን  ጉንፋን  መሰል ወረርሽኝ  ተከትሎ በአንዳንድ ተቋማት  በተደረገ  ምርመራ አስከ 86 በመቶ የሚሆኑት ኮቪድ  እንደተገኘባቸው የኢትዮጵያ  ህብረተሰብ ኢኒስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ኢኒስቲትዩቱ ባለፉት 15 ቀናትም በተለይ በአዲስ አበባ የኮቪድ-19 ስርጭት በስፋት መስተዋሉን ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡:

በዚህም ኢኒስቲትዩቱ  ባደረገው ቅኝትና  ከአንዳንድ ተቋማት በወሰደው ናሙና  ከ59 እስከ 86 በመቶ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ወደጤና ተቋማት  ሂደው ከተመረመሩት ከ55ሺ በላይ ሰዎች ከ25 ሺ በላይ የሚሆኑት ኮቪድ-19 እንዳለባቸው ኢኒስቲትዩቱ አመልክቷል፡፡

እንደአገር ከሁለት ሳምንት በፊት 5 በመቶ የነበረው በኮቪድ 19 የመያዝ ምጣኔ አሁን ላይ ወደ 36  በመቶ ከፍ ማለቱንም መረጃው አመልክቷል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ  “የጉንፋን ወረረሽኝ” ከሚለው መዘናጋት ወጥቶ  የኮቪድ 19 መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ከቫይረሱ መጠበቅ  እንደሚገባ  አስገንዝቧል፡፡

የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተለይም ትምህርት  ቤት እና መሰል መስሪያ ቤቶች ጥብቅ የሆነ ኮቪድ መከላከያ ፕሮቶኮል እንዲተገብሩም ኢኒስቲትዩቱ  በመግለጫው አሳስቧል፡፡

ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply