በአጣዬና ማጀቴ አካባቢ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት እንዲቆም ለክልሉና ለፌደራል መንግስት ጥሪ ቢቀርብም በአፋጣኝ ምላሽ ማግኘት እንዳልተቻለ የኤፍራታ እና ግድም ወረዳ  የሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በአጣዬና ማጀቴ አካባቢ ከዛሬ ሳንምት ጀምሮ በንጽሁን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ባለው  ጥቃት በርካቶች ሲሞቱ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ዜጎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና   እንደተፈናቀሉም ተገልጿል፡፡የኤፍራታ እና ግድም ወረዳ የሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን አልታዬ ለአሐዱ እንደተናገሩት ጥቃቱ ከተጀመረ 8 ቀናት የተቆጠረ ሲሆን በተለይም የጸጥታ ኃይሎች የማይደርሱበት ቦታ ላይ በመዟዟር ንጽሀን ላይ ግድያና ንብረት በማውደም ህገ-ወጥ ድርጊት እየተፈጸመ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሰርግ ነው በሚል ምክንያት በጊሌ ጥሙጋ ወረዳ በተጀመረው ግጭት አንድ ሰው ሲሞት 2 ሰዎች ደግሞ የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል፤ ግጭቱ ይበልጥ እንዳይባባስ በሚል ለዞን፣ ለክልልና ለፌደራል መንግስት ማስታወቃቸውን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡አክለውም ጥቃት አድራሾቹ  የተደራጁና  የታጠቁ ኃይሎች በመሆናቸው አካባቢውን ዙሪያውን በመክበብ መትረየስ፣ ብሬን እንዲሁም ቦንብ የመሳሰሉ መሳሪያዎችን በመጠቀም በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት በማድረሳቸው በማህበረሰቡ ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት ቢያደርግም ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ምክንያት ግጭቱን በወቅቱ ማርገብ አለመቻሉን ገልፀዋል፡፡የታጠቁት ኃይሎች እድሜቸው ከ8 እስከ 15 ዓመት ያሉ የአማራ ተወላጆችን እየመረጡ እየገደሉ ነው ያሉት አቶ ሰለሞን ድርጊቱን ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ነው ብለውታል፡፡

እየተፈጸመ ያለውን  ጥቃት  እንዲያስቆሙላቸው ለክልሉና ለፌደራል መንግስት ጥሪ ቢቀርምብ  በአፋጣኝ  ምላሽ ማግኘት እንዳልተቻለ የተናገሩት አቶ ሰለሞን አሁንም ድረስ የተወሰነ መረጋጋቶች ቢኖርም የጸጥታ ኃይሎች የማይደርሱበት ቦታ ጥቃቱ እንደቀጠለ ነው ብለዋል፡፡በጥቃቱም በርካቶች ህይወታቸው አልፏል፤ ቆስለዋልም፤ ይሁን እንጅ አሁን ላይ የተጎጂዎችን ቁጥር ይህ ነው ብሎ ለመግለጽ አስቸጋሪ እንደሆነ ተገልፃል፡፡

ቀን 18/07/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply