በአጭበርባሪዎች  ምክንያት እውነተኛ የኩላሊት ታማማዊች  የማህበረሰቡን እርዳታ እየተነፈጉ ነው ተባለ።የኩላሊት ህመምተኞች  እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ  አቶ ሰለሞን አሰ…

በአጭበርባሪዎች  ምክንያት እውነተኛ የኩላሊት ታማማዊች  የማህበረሰቡን እርዳታ እየተነፈጉ ነው ተባለ።

የኩላሊት ህመምተኞች  እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ  አቶ ሰለሞን አሰፋ
እውነተኛ የኩላሊት ተማሚ ሳይሆኑ በሚያጭበረብሩ ሰዎች ምክንያት ማህበረሰቡ ትክክለኛ ተማሚውን እየረዳ እንዳልሆነ ነግረውናል፡፡

በተለይም ተሽከርካሪን በመጠቀም የሚደረጉ  የእርዳታ ጥሪዎች አሁን ላይ  በአጭበርባሪዎች የተነሳ  የኩላሊት ተማሚዎች በማህበረሰቡ ዘንድ  እምነት እያጡ  እየመጡ  እና ለሌላ ወጪ እየደረጋቸው እንደሆነ  ገልፀዋል።

እውነተኛ የኩላሊት ተማሚዎች መኪናን በመጠቀም  እርዳታ እንዲያገኙ የማህበሩ እና የፖሊስ ማረጋገጫ  እንዲሁም ልዩ ፍቃድ እንዲይዙ እያደረጉ እንደሆነም ተናግረዋል።

በዚህም አጭበርባሪዎች  እንዲያዙ እና እርዳታው ለትክክለኛው የህመሙ ታማሚ ሰው እንዲደርስ ከፖሊስ ጋር በመሆን ስራዎችን እየሰሩ እንደሆነ አንስተዋል ።

እርዳታ ለመጠየቅም  ታማሚዎች ልዩ ፍቃድ መያዝ እንዳለባቸው  ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ብቻ ወደ 3ሺ የሚጠጋ  የኩላሊት ህመምተኛ አለ የሚሉት አቶ ሰለሞን

ከነዛ ውስጥም ወደ 2 መቶ የሚሆኑት  ነፃ ህክምና የሚያገኙና 45 ደግሞ በግማሽ ህክምና እንደሚገኝ አስታውቀዋል ።

የተቀረው ከ2ሺ አምስት መቶ  በላይ ታማሚ ግን በራሱ እና በመኪና እና በመሰል የእርዳታ ገንዘብ እንደሚኖሩ ገልፀዋል።

ስለሆነም እርዳታ የሚያረጉ ማህበረሰብ ታማሚውን በቅርበት አረጋግጠው እንዲረዱ አቶ ሰለሞን   ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

ለአለም አሰፋ
ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply