የልኡካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡

የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቀሌ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን፥ ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ታምኖበታል።
በልዑካን ቡድኑ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት መካተታቸውንም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 17ቀን 2015 ዓ.ም
Source: Link to the Post