በአፋር እና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ውይይት ተካሄደ

በአፋር እና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል እና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን አጎራባች አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም የምክክር መድረክ በሰመራ ተካሄደ ፡፡
በአፋር ክልል እና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን አጎራባች ዞን እና ወረዳዎች አካባቢ የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሁለቱም ህዝቦች የአመራር አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጎሳ እና የሀይማኖት መሪዎች በተገኙበት የሰላም የምክክር መድረክ በሰመራ ተካሂዷል፡፡
በምክክር መድረኩ የሁለቱን ህዝቦች ሁለንተናዊ ቀረቤታ የሚዳስስ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት እና ምክክር ተደርጓል፡፡
የአፋር ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ሁመድ ሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች ትስስራቸው የጠነከረ አንድ ህዝቦች እና ቤተሰብም ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በአጎራባች አካባቢዎቻችን የተፈጠሩ ግጭቶችን በማስቆም ህዝቡን የሰላም እና የልማት ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን የከሚሴ ዞን አአስተዳደር አቶ አህመድ ሀሰን በበኩላቸው ግጭቶቹን ለመፍታት ትኩረት በመስጠት ህዝቡን የሚወክል አመራር ለመስጠት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት የሚያጠናክሩ ስራዎችን ማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ተሳታፊ የሆኑ የአመራር አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጎሳ እና የሀይማኖት መሪዎች የችግሩ መነሻ ከሆኑት ውስጥ የአመራር ችግር፣ የመሬት ወረራ እና ህገ ወጥ ንግድ እንዲሁም የእንስሳት ስርቆቶች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል፡፡
በሌላ በኩል በሁለቱም በኩል ችግሩን የሚያባብሱት ጥገኛ አክቲቪስቶች፣ አንዳንድ አመራሮች እና የጸረ ሰላም አስፈጻሚ ጥቅመኛ ግለሰቦች በተለይ ከጁንታው ጋር ትስስር ያላቸው መሆኑን በመጥቀስ የመፍትሄ ሀሳብም አቅርበዋል፡፡
በቀጣይ ግጭቱን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገር ሽማግሌዎች ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ችግሩን ከአመራር አካላት ጋር በጋራ ለመፍታት ቃል መገባቱን የአፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት የላከልን መግለጫ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በአፋር እና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ውይይት ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply