በአፋር እና በኢሳ ሶማሌዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት

https://gdb.voanews.com/506DED22-8854-4373-BC53-1AE36F211707_cx0_cy22_cw0_w800_h450.jpg

የሶማሌ ክልል መንግሥት ሰሞኑን በአፋር እና በኢሳ ሶማሌዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት መንስዔ በሁለቱ ክልሎች አስቀድሞ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በጣሰ መልኩ ሰፈራ በተከለከለበት ቦታ ሰፈራ በመጀመሩ ነው ብሏል።

የአፋር ክልል በበኩሉ ያሰፈርኳቸው ሰዎች በጎርፍ የተፈናቀሉ ናቸው ብሏል። የሶማሌ ክልል የአፋር ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 27 ሰላማዊ የኢሳ ሶማሌዎች ተገድለዋል ሲል የአፋር ክልል በበኩሉ በኢሳ ሶማሌዎች 8 ሰዎች ተገድለውብኛል ሲል ቅሬታውን አቅርቦ ነበር። ባለፈው ማክሰኞ የትምህርት ሚኒስቴር ባልደረቦች መገደላቸውን ተከትሎ የመከላከያ ሚኒስቴር በገዳማይቱ ወይም ገርበኢሴ ቀበሌዎች ገብቶ የነበረውንሚና የሶማሌ ክልል ተችቶታል።

በትላንትናው ዕለትም በሲቲ ዞን በርካታ ወረዳዎች የመከላከያ ሰራዊትን ሚና የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply