በአፋር ክልል መጋሌ ወረዳ የምግብ እጥረት ለሞት የሚዳርግ የጤና ችግር እንዳስከተለ ተገለጸ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-63cd-08dbbe007a3d_tv_w800_h450.jpg

በአፋር ክልል ኪልባቲረሱ ዞን መጋሌ ወረዳ፣ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ማጋጠሙን፣ ወረዳው አስታወቀ፡፡

ከምግብ እጥረቱ ጋራ ተያይዞ በሚፈጠር የጤና ችግርም፣ የሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ መሐመድ ዲሚስ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ከወረዳው ነዋሪ 70 በመቶው፣ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የጠቆሙት ምክትል አስተዳዳሪው፣ ችግሩ ዐቅም በላይ እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

የመጋሌ ጤና ጣቢያ ሓላፊ ኑሩ ሙሳም፣ ወደ ጤና ተቋሙ ለሕክምና ከሚመጡት ውስጥ ከ40 በመቶ የሚልቁት፣ ከምግብ እጥረት ጋራ የተያያዘ የጤና ችግር እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

የምግብ እጥረቱ ዓለም አቀፍ ለጋሾች ርዳታ ማቅረባቸውን ካቆሙ በኋላ እንደተባባሰ የጠቆሙት የአፋር አርብቶ አደሮች ልማት ማኅበር ፕሮግራም ዲሬክተር ቫለሪን ብራውን፣ የአገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ አካላት ትኩረት እንደሚያሻው አሳስበዋል፡፡

ዘገባውን ያጠናቀረው መስፍን አራጌ ነው። አሉላ ከበደ በድምፅ አንብቦታል።

ዘገባውን ለማድመጥ የተያያዘውን ፋይል ይከታተሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply