You are currently viewing በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በድንገት በተከሰተ  የእሳት ቃጠሎ ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች ወደሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ሚያዝያ 3 ቀን 2014 ዓ.ም…

በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በድንገት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች ወደሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 3 ቀን 2014 ዓ.ም…

በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በድንገት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች ወደሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በድንገት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ በግምት ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያቤቶች መውደማቸውን የወረዳው አስተዳድር ገልፀዋል። የሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ አስተዳድር አቶ ሀሰን ሀንዲ ለአፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት በስልክ እንደገለፁት የእሳት ቃጠሎ አደጋው የደረሰው ወደ 10 :00 ሰዓት አካባቢ በድንገት ከቤንዝል መሸጫ ቤት በመነሳት መሆኑን ጠቁመዋል። በደረሰው ድንገተኛ የቃጠሎ አደጋም ወደፊት የሚጣራ ሁኖ በግምት ግን ከ80 በላይ መኖሪያ ቤቶች እንደዚሁም ወደ 80 ሊጠጋ የሚችል የተለያዩ የንግድ ሱቆች በእሳት አደጋው የወደሙ ሲሆን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ አደጋ ግን የለም ብለዋል። በአካባቢው ከነበረው ከፍተኛ ንፋስ መኖሩ የተነሳ እና የውሀ እጥረት በመኖሩ ቃጦሎው በፍጥነት በመባባሱ ምክንያትም እሳቱን ለመቆጣጠር ባለመቻሉ ከፍተኛ ውድመት ተከስቷል ሲሉ የወረዳው አስተዳደር አስታውቀዋል። ስለሆነም በቅድሚያ እሳቱን በማጥፋት እና ለተጎጂዎቹ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ ሀሰን ሀንዲ በመጨረሻም ባስተላለፉት መልዕክት በብዛት የቤንዚል ሽያጭ ከሚከናወንበት ቦታ በቀላሉ የእሳት አደጋ እየተፈጠረ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል ሲል የዘገበው የአፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply