በአፋር ክልል በቀጠለው ውጊያ ሳቢያ 100 ሺህ ያህል የክልሉ ነዋሪዎች ከቀያቸው እንደተፈናቀሉ መረጃዎች አመለከቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲ…

በአፋር ክልል በቀጠለው ውጊያ ሳቢያ 100 ሺህ ያህል የክልሉ ነዋሪዎች ከቀያቸው እንደተፈናቀሉ መረጃዎች አመለከቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ 76 ሺህ ያህሉ ተፈናቃዮች በዘጠኝ ጊዜያዊ መጠለያዎች ተጠልለው ይገኛሉ። ከትግራይ ጋር በሚዋሰኑት የአፋር ወረዳዎች ሕወሃት ከክልሉ ልዩ ኃይሎችና መከላከያ ሠራዊት ጋር ውጊያ ሲጀምር በተለያዩ ቦታዎች ተደብቀው የቆዩ ተፈናቃዮች አሁን ወደ ጊዜያዊ መጠለያዎች እየገቡ እንደሆነ ተነግሯል። ሆኖም ተፈናቃዮቹ እያገኙት ያለው የምግብ ዕርዳታ በጣም ውስን እንደሆነ የክልሉ አደጋ መከላከልና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቢሮ የጠቀሰ ሲሆን፣ ተጨማሪ ዕርዳታ ካልተገኘ አስከፊ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል አስጠንቅቋል ሲል ዋዜማ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply