በአፍዴራ እና በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች በርሀብ ምክንያት ዜጎች አየሞቱ ይገኛሉ ነው ያሉት።
ከጦርነት ማብቃት በኋላ መንግስት የአፋር ክልል ህዝብን ዞር ብሎ አላየም ይህ በመሆኑም ህዝቡ ለዘርፈ ብዙ ችግር መጋለጡን ነው የተነገረው።
የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራል መንግስት የክልሉን ህዝብ እረስተውታል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ።
በክልሉ ያሉ አመራሮች በህገወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ በመሰማራታቸው ህጋዊ ሆኖ መስራት ወንጀል እየሆነ ነው ብለዋል።
በተለይም የክልሉ ሀላፊዎች የጨው ምርት ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ዜጎች ክንዳቸው እያሳረፉ እንደሚገኙ ነው ዜጎች የተናገሩት።
አሁን ላይ በክልሉ በጨው ምርት መሰማራት ከባድ መሆኑን የሚናገሩት ዜጎች ሁሉም ነገር በሙስና ሆኗል ብለዋል።

በክልሉ በጨው ምርት ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው የዶቢ የጨው አምራቾች ማህበር በክልሉ መንግስት ቅሬታውን አሰምቷል።
ማህበሩ ባልታወቀ ምክንያት ስራው እንዲያቆም ከክልሉ የማእድን ቢሮ ተነግሮታል።
ማህበሩ ይህ ውሳኔ ድንጋጤ እንደፈጠረበት አስታውቆ የክልሉ ማእድን ልማት ቢሮ ሀላፊዎች አምራቾችን በራሳቸው ሰዎች ለመተካት የወጠኑት ሴራ ነው ሲሉ የማህበሩ አባላት ተናግረዋል።
በክልሉ ጨው አምራቾች ምርታቸው የሸጡበት የ6ወር ክፍያም እንዳልተከፈላቸው ተናግረዋል።
በክልሉ የጨው አምራች ማህበራት በግለሰቦች እና በመንግስት ሀላፊዎች እየተዘወረ ይገኛል ብለዋል።
የጨው ምርት እና ጅምላ አከፋፋዮችም የባለስልጣን ቤተቦች ሠሆናቸውን የተናገሩት የዶቢ ጨው አምራች ማህበር አሁን ላይ ችግር ላይ መውደቁን ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት በጨው ጉዳይ ቅሬታ የሚያነሱ ዜጎችን ለእንግልት እየዳረገ እና እያሰረ እንደሚገኝ ነው ማህበራቱ የተናገሩት።
በመሆኑም የፌደራል መንግስት የችግሩን ግዝፈት ተረድቶ መፍትሔ እንዲሰጣቸው የማህበሩ አባላት ተናግረዋል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post