በአፋር ክልል ትምህርት ቤቶችን በመጎብኘት ላይ የነበሩ ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ዐስታወቀ።  /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 18/201…

በአፋር ክልል ትምህርት ቤቶችን በመጎብኘት ላይ የነበሩ ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ዐስታወቀ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 18/201…

በአፋር ክልል ትምህርት ቤቶችን በመጎብኘት ላይ የነበሩ ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ዐስታወቀ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// አቶ ሙላት ጸጋዬ እና አቶ አባባው አያልነው የተባሉ ሁለት ሰዎች ትናንት ማክሰኞ በአፋር ክልል በሥራ ላይ እያሉ «ያልታወቊ» በተባሉ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው ማለፉን ሚኒስቴሩ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ባወጣው በዚሁ የሐዘን መግለጫ መልዕክቱ የግለሰቦቹን በታጣቂዎች መገደል ከመግለጽ ውጭ እንዴት እንደተገደሉ እና ግድያው የተፈጸመበትን ትክክለኛ ቦታ አልገለጸም። የትምህርት ሚንስትር ሚኒስትሩ ጌታጉን መኩሪያ (ዶ/ር) በሠራተኞቹ ኅልፈት «የልብ ሐዘንና ስብራት» እንደተሰማቸው በቲዊተር ማኅበራዊ የመገናኛ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። በአፋር ክልል አልፎ አልፎ በታጠቁ ኃይሎች በሚደርሱ ጥቃቶች ከዚህ ቀደምም የሰዎች ሕይወት ማለፉ ሲዘገብ ቆይቷል። DW Amharic

Source: Link to the Post

Leave a Reply