በአፍሪካ ሀገራት እየተሰባባሱ የመጡ ግጭት የኮሮና ቫይረስን እንዲስፋፋ ምክንያት እየሆኑ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ፡፡

በአፍሪካ ከሰህራ በታች ባሉ አካባቢዎች በታጠቁ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ግጭቶች የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን የከፋ እንዲሆን አድርገዋል ብሏል፡፡

ድርጅቱ ባወጣው ዘገባ  ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አካባቢዎች  በመንግስታቶቹ እና በታጠቁ ቡድኖች መካከል ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል ያለ ሲሆን  በማሳያነትም በደቡባዊ አፍሪካ በሞዛንቢክ ካቦ ዴልጋዶ አወራጃ እንዲሁም በኢትዮጵያ  ሰሜናዊ ክፍል በሚገኘው በትግራይ ክልል ግጭቶች መከሰታቸው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አሁን ካለው በላይ በባሰ ሁኔታ  እንዲባባስ እድል እየፈጠረ ነው ብሏል፡፡

ሪፖርቱ አክሎም ኮሮና ቫይረስ መባባሱ ብሎም ግጭቶች መኖራቸው ደግሞ በብዙ ሀገራቶች ውስጥ ቀድሞውኑ አስጊ የነበረውን የስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች  አያያዝ ላይ ችግር ከመፍጠሩም  ባሻገር  አስፈላጊ አቅርቦቶች ከድንበር አካባቢ  ለማጓጓዝ መዘግየት ያጋጥማል  ሲል ጅርጅቱ ተናግሯል፡፡ከባድ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ከኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ባለፈ ፆታዊ ጥቃቶችም  ጨምረዋል ብሏል አምነስቲ በሪፖርቱ ፡፡ ምንጭ፡- አናዶሉ ነው፡፡

ቀን 30/07/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

The post በአፍሪካ ሀገራት እየተሰባባሱ የመጡ ግጭት የኮሮና ቫይረስን እንዲስፋፋ ምክንያት እየሆኑ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply