በአፍሪካ ቀንድ ከ58 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ ዋስትና እጦት ተጋርጦባቸዋል ተባለ፡፡በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ 58.1 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ዋስትና እጦት አለባቸው ሲሉ የተባበሩት መንግስታት…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/ciHdmIB0k_5wK4OQ7Or4KRCGfDsildK2Bj310Th_no6Eq3_BNLhLeOg1o3g3eEefFhn-XfVBpbKVlfU0be0YmZg2rR28M3CwiOGhGeBt8zrSUwlG-9tVMwKaGApszUl6saTvdx2bpkyikZdI83Q-yWE0gv-ImTLa6iXKPJvC4Z9A1yi8634euaaCh4N-M79Dqm_jHEMGDMtU0mgFZDZv3FJCD1TITu7qAktHjo_syUmeeeXM-sZ1FlRakrhwzCcLXCse5kpR1bMBHkIixrGMob40dB3E6TEod0f2gr_IQdUQF0SDJpiqgmQjPTvrmZ-dqHC-OFOvB5hhI0QxXp7e8g.jpg

በአፍሪካ ቀንድ ከ58 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ ዋስትና እጦት ተጋርጦባቸዋል ተባለ፡፡

በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ 58.1 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ዋስትና እጦት አለባቸው ሲሉ የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ይፋ ባደረጉት የጋራ ሪፖርት አስታውቀዋል።

ከስምንቱ የኢጋድ አባል ሀገራት ጅቡቲ፣ኬንያ፣ሶማሊያ፣ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን እና ኡጋንዳ 30 ነጥብ 5 ሚሊየን ያህሉ የተውጣጡ መሆናቸውን ፋኦ እና ኢጋድ በሪፖርታቸው አሳውቀዋል።

የተቀሩት 27.6 ሚሊዮን ሰዎች ከቡሩንዲ፣ ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ከታንዛኒያ የመጡ መሆናቸው ተነስቷል

አብዛኛው የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው (23.4 ሚሊዮን) በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ሱዳን 17.7 ሚሊዮን እና ደቡብ ሱዳን 4 ሚሊዮን መሆናቸውን FAO እና ኢጋድ ገልጸዋል።

ከምግብ ቀውስ በተጨማሪ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በተለያዩ በሽታዎች እየተባባሰ እንደሚገኝ፣ ከእነዚህም መካከል ኮሌራ፣ ወባ፣ እና ኩፍኝ ይገኙበታል

የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ ማዕከል የአፍሪካ ቀንድ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባለው ጊዜ ውስጥ ከባድ ዝናብ ስለሚኖረው በጎርፍ ሳቢያ የምግብ ቀውሱ በአንዳንድ ሀገራት ሊቀጥል ይችላልም ብለዋል።

በለዓለም አሰፋ

የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply